Logo ng YouVersion
Hanapin ang Icon

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 6

6
ወደ ጥብ​ር​ያ​ዶስ ስለ መሄዱ
1ከዚህ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ወደ ጥብ​ር​ያ​ዶስ ሄደ። 2በበ​ሽ​ተ​ኞ​ችም ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት ስለ አዩ ብዙ ሰዎች ተከ​ተ​ሉት፤ 3ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ተራራ ወጣ፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ጋር በዚያ ተቀ​መጠ። 4የአ​ይ​ሁድ የፋ​ሲካ በዓ​ልም ቀርቦ ነበር።
አም​ስ​ቱን እን​ጀ​ራና ሁለ​ቱን ዓሣ ስለ ማበ​ር​ከቱ
5ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ሲመጡ አየና ፊል​ጶ​ስን፥ “ለእ​ነ​ዚህ ሰዎች የም​ና​በ​ላ​ቸው እን​ጀራ ከወ​ዴት እን​ግዛ?” አለው። 6ሲፈ​ት​ነው ይህን አለ እንጂ፥ እር​ሱስ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ያውቅ ነበር። 7ፊል​ጶ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “ከእ​ነ​ርሱ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጥቂት ጥቂት ይወ​ስዱ ዘንድ የሁ​ለት መቶ ዲናር እን​ጀራ አይ​በ​ቃ​ቸ​ውም።” 8ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አንዱ የስ​ም​ዖን ጴጥ​ሮስ ወን​ድም እን​ድ​ር​ያስ እን​ዲህ አለው፥ 9“አም​ስት የገ​ብስ እን​ጀ​ራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላ​ቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን እነ​ዚህ ይህን ለሚ​ያ​ህል ሰው ምን ይበ​ቃሉ?” 10ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሰዎ​ቹን እን​ዲ​ቀ​መጡ አድ​ርጉ” አለ፤ የዚያ ቦታም ሣሩ ብዙ ነበር፤ ወን​ዶ​ቹም በመ​ስኩ ላይ ተቀ​መጡ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም አም​ስት ሺህ ያህል ነበር። 11ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን እን​ጀራ ይዞ አመ​ሰ​ገነ፤ ቈር​ሶም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሰጣ​ቸው፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ለተ​ቀ​መ​ጡት ሰዎች ሰጡ​አ​ቸው፤#“ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሰጣ​ቸው ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ለተ​ቀ​መ​ጡት ሰጡ​አ​ቸው” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ የለም። ከዓ​ሣ​ውም እን​ዲሁ የፈ​ለ​ጉ​ትን ያህል ሰጡ​አ​ቸው። 12ከጠ​ገ​ቡም በኋላ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን፥ “ከቍ​ር​ስ​ራሹ ምንም የሚ​ወ​ድቅ እን​ዳ​ይ​ኖር የተ​ረ​ፈ​ውን ቍር​ስ​ራሽ አንሡ፤” አላ​ቸው። 13እነ​ር​ሱም ሰበ​ሰቡ፥ በል​ተው ከጠ​ገቡ በኋ​ላም ከአ​ም​ስቱ የገ​ብስ እን​ጀራ የተ​ረ​ፈው ቍር​ስ​ራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሞላ። 14ሕዝ​ቡም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት አይ​ተው፥ “ይህ በእ​ው​ነት ወደ ዓለም የሚ​መ​ጣው ነቢይ ነው” አሉ። 15ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መጥ​ተው ነጥ​ቀው ሊያ​ነ​ግ​ሡት እን​ደ​ሚሹ ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና ብቻ​ውን ወደ ተራራ ሄደ።
በባ​ሕር ላይ ስለ መሄዱ
16በመ​ሸም ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ወደ ባሕር ወረዱ። 17ወደ ታን​ኳም ወጡ፤ ወደ ባሕር ማዶ ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆ​ምም ሄዱ፤ እነ​ሆም፥ ፈጽሞ ጨለማ ሆነ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ እነ​ርሱ ገና አል​መ​ጣም ነበር። 18ባሕሩ ግን ይታ​ወክ ነበር፤ ጽኑ ነፋስ ይነ​ፍስ ነበ​ርና። 19ሃያ አም​ስት ወይም ሠላሳ ምዕ​ራፍ ያህል ከሄዱ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በባ​ሕር ላይ ሲሄድ አዩት፤ ወደ ታን​ኳዉ በቀ​ረበ ጊዜም ፈሩ። 20እር​ሱም፥ “እኔ ነኝ፤ አት​ፍሩ” አላ​ቸው። 21ወደ ታን​ኳ​ው​ዪቱ ሊያ​ወ​ጡት ሲሹም ታን​ኳ​ዪቱ ወዲ​ያ​ውኑ ሊሄዱ ወደ ወደ​ዱ​በት ወደብ ደረ​ሰች። 22በማ​ግ​ሥ​ቱም ከባ​ሕሩ ዳር ቆመው የነ​በሩ ሰዎች ከአ​ን​ዲት ታንኳ በቀር ከዚያ ሌላ ታንኳ እን​ዳ​ል​ነ​በረ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ለብ​ቻ​ቸው ሄዱ እንጂ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ ታንኳ እን​ዳ​ል​ወጣ አዩ። 23ደግ​ሞም ጌታ​ችን የባ​ረ​ከ​ውን እን​ጀራ ከበ​ሉ​በት ቦታ አቅ​ራ​ቢያ ከጥ​ብ​ር​ያ​ዶስ ሌሎች ታን​ኳ​ዎች መጥ​ተው ነበር። 24እነ​ዚያ ሰዎ​ችም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም በዚያ እን​ዳ​ል​ነ​በሩ ባዩ ጊዜ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይፈ​ል​ጉት ዘንድ በእ​ነ​ዚያ ታን​ኳ​ዎች ገብ​ተው ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም መጡ። 25በባ​ሕሩ ዳርም ባገ​ኙት ጊዜ፥ “መም​ህር ሆይ፥ ወደ​ዚህ መቼ መጣህ?” አሉት።
ስለ ሕይ​ወት ምግብ
26ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ንተ የም​ት​ፈ​ል​ጉኝ እን​ጀራ ስለ በላ​ች​ሁና ስለ ጠገ​ባ​ችሁ ነው እንጂ ተአ​ም​ራት ስለ አያ​ችሁ አይ​ደ​ለም። 27የሰው ልጅ ለሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ለሚ​ኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚ​ጠ​ፋው መብል አይ​ደ​ለም፤ ይህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ አት​ሞ​ታ​ልና።” 28“እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ እን​ሠራ ዘንድ ምን እና​ድ​ርግ?” አሉት። 29ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ይህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ እርሱ በላ​ከው ታምኑ ዘንድ ነው፤” አላ​ቸው።
ምል​ክት ስለ መጠ​የ​ቃ​ቸው
30እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉት፥ “የም​ት​ሠ​ራ​ውን አይ​ተን በአ​ንተ እና​ምን ዘንድ ምን ተአ​ም​ራት ታደ​ር​ጋ​ለህ? 31#ዘፀ. 16፥4፤ 15፤ መዝ. 77፥24። አባ​ቶ​ቻ​ች​ንስ ‘ሊበሉ እን​ጀራ ከሰ​ማይ ሰጣ​ቸው’ ተብሎ እንደ ተጻፈ በም​ድረ በዳ መና በሉ። 32ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ያን እን​ጀራ ከሰ​ማይ የሰ​ጣ​ችሁ ሙሴ አይ​ደ​ለም፤ አባቴ ከሰ​ማይ የእ​ው​ነት እን​ጀ​ራን ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል እንጂ። 33የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ጀራ ከሰ​ማይ የሚ​ወ​ርድ፤ ለዓ​ለ​ምም ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ ነውና።” 34እነ​ር​ሱም፥ “አቤቱ ከዚያ እን​ጀራ ሁል​ጊዜ ስጠን” አሉት።
ስለ ሕይ​ወት ኅብ​ስት
35ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሕ​ይ​ወት እን​ጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚ​መጣ ከቶ አይ​ራ​ብም፤ በእኔ የሚ​ያ​ም​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም። 36ነገር ግን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አያ​ች​ሁኝ፤ አላ​መ​ና​ች​ሁ​ብ​ኝ​ምም። 37አብ የሚ​ሰ​ጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመ​ጣል፤ ወደ እኔ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም ከቶ ወደ ውጭ አላ​ወ​ጣ​ውም። 38ከሰ​ማይ የወ​ረ​ድሁ የላ​ከ​ኝን ፈቃድ እንጂ፥ ፈቃ​ዴን ላደ​ርግ አይ​ደ​ለ​ምና። 39የላ​ከኝ የአብ ፈቃ​ድም ይህ ነው፤ ከሰ​ጠኝ ሁሉ አን​ድስ እንኳ ቢሆን እን​ዳ​ይ​ጠፋ ነው፤ ነገር ግን እኔ በኋ​ለ​ኛ​ዪቱ ቀን አስ​ነ​ሣ​ዋ​ለሁ። 40የአ​ባቴ ፈቃዱ ይህ ነው፤ ወል​ድን አይቶ የሚ​ያ​ም​ን​በት ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኝ ነው፤ እኔም በመ​ጨ​ረ​ሻ​ዪቱ ቀን አስ​ነ​ሣ​ዋ​ለሁ።”
ስለ አይ​ሁድ ማን​ጐ​ራ​ጐር
41አይ​ሁ​ድም ስለ እርሱ አን​ጐ​ራ​ጐሩ፤ “ከሰ​ማይ የወ​ረደ የሕ​ይ​ወት እን​ጀራ እኔ ነኝ” ብሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና። 42“እኛ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን የም​ና​ው​ቃ​ቸው ይህ የዮ​ሴፍ ልጅ ኢየ​ሱስ አይ​ደ​ለ​ምን? እን​ግ​ዲህ እን​ዴት ከሰ​ማይ ወረ​ድሁ ይለ​ናል?” አሉ። 43ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እርስ በር​ሳ​ችሁ አታ​ን​ጐ​ራ​ጕሩ። 44የላ​ከኝ አብ ካል​ሳ​በው በቀር ወደ እኔ መም​ጣ​ትን የሚ​ችል የለም፤ እኔም በመ​ጨ​ረ​ሻ​ዪቱ ቀን አስ​ነ​ሣ​ዋ​ለሁ። 45#ኢሳ. 54፥13። ‘ሁሉም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ማሩ ይሆ​ናሉ’ ተብሎ በነ​ቢ​ያት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል፤ እን​ግ​ዲህ ከአ​ባቴ የሰማ ሁሉ ተምሮ ወደ እኔ ይመ​ጣል። 46ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው በቀር አብን ያየው ማንም የለም፤ እር​ሱም አብን አየው። 47እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በእኔ የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት አለው። 48የሕ​ይ​ወት እን​ጀራ እኔ ነኝ። 49አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁስ በም​ድረ በዳ መና በሉ፥ ሞቱም። 50ከእ​ርሱ የበላ ሁሉ እን​ዳ​ይ​ሞት ከሰ​ማይ የወ​ረደ እን​ጀራ ይህ ነው።”
ስለ ሥጋ​ውና ስለ ደሙ
51“ከሰ​ማይ የወ​ረደ የሕ​ይ​ወት እን​ጀራ እኔ ነኝ፤ ከዚህ እን​ጀራ የሚ​በላ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፤ ስለ ዓለም ሕይ​ወት የም​ሰ​ጠው ይህ እን​ጀራ ሥጋዬ ነው።”
52አይ​ሁ​ድም፥ “ይህ እን​በላ ዘንድ ሥጋ​ውን ሊሰ​ጠን እን​ዴት ይች​ላል?” ብለው እርስ በር​ሳ​ቸው ተከ​ራ​ከሩ። 53ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ የሰ​ውን ልጅ ሥጋ ካል​በ​ላ​ችሁ፥ ደሙ​ንም ካል​ጠ​ጣ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የላ​ች​ሁም። 54ሥጋ​ዬን የሚ​በላ፥ ደሜ​ንም የሚ​ጠጣ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት አለው፤ እኔም በኋ​ለ​ኛ​ዪቱ ቀን አነ​ሣ​ዋ​ለሁ። 55ሥጋዬ እው​ነ​ተኛ መብል ነውና፤ ደሜም እው​ነ​ተኛ መጠጥ ነውና። 56ሥጋ​ዬን የሚ​በላ፥ ደሜ​ንም የሚ​ጠጣ በእኔ ይኖ​ራል፤ እኔም በእ​ርሱ እኖ​ራ​ለሁ። 57የላ​ከኝ አብ ሕያው እንደ ሆነ፥ እኔም ስለ አብ ሕያው ነኝ፤ ሥጋ​ዬ​ንም የሚ​በላ እርሱ ደግሞ ስለ እኔ ሕያው ሆኖ ይኖ​ራል። 58ከሰ​ማይ የወ​ረደ እን​ጀራ ይህ ነው፤ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ በል​ተ​ውት እን​ደ​ሞ​ቱ​በት ያለ መና አይ​ደ​ለም፤ ይህን እን​ጀራ የሚ​በላ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕያው ሆኖ ይኖ​ራል።” 59በቅ​ፍ​ር​ና​ሆ​ምም በም​ኵ​ራብ ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው ይህን ተና​ገረ፤
ስለ ተጠ​ራ​ጠ​ሩት ሰዎች
60ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ብዙ​ዎቹ ይህን ሰም​ተው፥ “ይህ ነገር የሚ​ያ​ስ​ጨ​ንቅ ነው፤ ማንስ ሊሰ​ማው ይች​ላል?” አሉ። 61ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ስለ​ዚህ ነገር እንደ አን​ጐ​ራ​ጐሩ በልቡ ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህ ያሰ​ና​ክ​ላ​ች​ኋ​ልን? 62እን​ግ​ዲህ የሰው ልጅ ቀድሞ ወደ ነበ​ረ​በት ሲያ​ርግ ብታ​ዩት እን​ዴት ይሆን? 63ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ መን​ፈስ ነው፤ ሥጋ ግን አን​ዳች አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ ይህም እኔ የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ቃል መን​ፈስ ነው፤ ሕይ​ወ​ትም ነው። 64ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ውስጥ የማ​ያ​ምኑ አሉ፤” ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከጥ​ንት ጀምሮ የማ​ያ​ም​ኑ​በት እነ​ማን እንደ ሆኑ፥ የሚ​ያ​ሲ​ዘ​ውም ማን እንደ ሆነ ያውቅ ነበ​ርና። 65እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ስለ​ዚህ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከአብ ካል​ተ​ሰ​ጠው በቀር ወደ እኔ መም​ጣት የሚ​ቻ​ለው የለም።”
66ስለ​ዚ​ህም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ወደ ኋላ​ቸው የተ​መ​ለሱ ብዙ​ዎች ናቸው፤ ከዚ​ያም ወዲህ አብ​ረ​ውት አል​ሄ​ዱም። 67ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዐሥራ ሁለ​ቱን፥ “እና​ንተ ደግሞ ልት​ሄዱ ትሻ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው። 68ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አቤቱ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም የሕ​ይ​ወት ቃል እያ​ለህ ወደ ማን እን​ሄ​ዳ​ለን? 69#ማቴ. 16፥16፤ ማር. 8፥29፤ ሉቃ. 9፥20። እኛስ የሕ​ያው#ግሪኩ እና አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ቅዱስ” ይላል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ክር​ስ​ቶስ አንተ እንደ ሆንህ አም​ነ​ናል፤ አው​ቀ​ና​ልም።” 70ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ እና​ን​ተን ዐሥራ ሁለ​ታ​ች​ሁን መር​ጫ​ችሁ የለ​ምን? ነገር ግን ከእ​ና​ንተ አንዱ ሰይ​ጣን ነው።” 71ይህ​ንም ስለ ስም​ዖን ልጅ ስለ አስ​ቆ​ሮ​ታ​ዊው ይሁዳ ተና​ገረ፤ እርሱ ያሲ​ዘው ዘንድ አለ​ውና፤ እር​ሱም ከዐ​ሥራ ሁለቱ አንዱ ነበር።

Haylayt

Ibahagi

Kopyahin

None

Gusto mo bang ma-save ang iyong mga hinaylayt sa lahat ng iyong device? Mag-sign up o mag-sign in