Logo ng YouVersion
Hanapin ang Icon

ዘፍጥረት 28

28
1ይስሐቅ ያዕቆብን አስጠርቶ ከመረቀው#28፥1 ወይም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ፣ እንዲህ ሲል አዘዘው፤
“ምንም ቢሆን ከነዓናዊት ሴት አታግባ። 2አሁኑኑ ተነሥተህ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ወደሚኖረው፣ ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ሂድ፤ እዚያም ከአጎትህ ከላባ ሴቶች ልጆች መካከል አንዲቷን አግባ። 3ሁሉን ማድረግ የሚችል አምላክ#28፥3 በዕብራይስጥ ኤልሻዳይ ማለት ነው። ይባርክህ፤ ብዙ ሕዝብ እስክትሆን ድረስ ልጆች አፍራ፤ ዘርህን ያብዛው። 4እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ለአብርሃም ሰጥቶ የነበረውን አንተም በስደት የምትኖርበትን ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ያወርስህ ዘንድ፣ ለአብርሃም የሰጠውን በረከት ለአንተና ለዘርህ ይስጥ።” 5ይስሐቅም ያዕቆብን በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ወደሚኖረው፣ የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም ወደ ሆነው ወደ ሶርያዊው የባቱኤል ልጅ ወደ ላባ ላከው።
6ዔሳው፣ ይስሐቅ ያዕቆብን መርቆ ሚስት እንዲያገባ ወደ ሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ እንደ ላከውና በባረከውም ጊዜ “ከነዓናዊት ሴት አታግባ” ብሎ ትእዛዝ እንደ ሰጠው ሰማ። 7ያዕቆብ የአባት የእናቱን ፈቃድ ለመፈጸም፣ ወደ መስጴጦምያ መሄዱንም ተረዳ። 8በዚህም የከነዓናውያን ሴቶች በአባቱ በይስሐቅ ዘንድ የቱን ያህል የተጠሉ መሆናቸውን ተገነዘበ፤ 9ስለዚህም ወደ እስማኤል ሄደ፣ የአብርሃም ልጅ እስማኤል የወለዳትን፣ የነባዮትን እኅት ማዕሌትን በሚስቶቹ ላይ ተጨማሪ አድርጎ አገባ።
ያዕቆብ በቤቴል ያየው ሕልም
10ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሥቶ ወደ ካራን ሄደ። 11ወደ አንድ ስፍራ እንደ ደረሰም ፀሓይዋ ጠልቃ ስለ ነበር፣ ዐዳሩን በዚያ አደረገ፤ በአቅራቢያው ከነበሩትም ድንጋዮች አንዱን ተንተርሶ ተኛ። 12በሕልሙም፣ ጫፉ ሰማይ የሚደርስ መሰላል በምድር ላይ ቆሞ፣ በላዩም የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ አየ። 13እግዚአብሔርም (ያህዌ) ከጫፉ ላይ#28፥13 ወይም በዚህ በአጠገቡ ቆሞ እንዲህ አለ፤ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ (ኤሎሂም)፣ የይስሐቅ አምላክ (ኤሎሂም) እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ፤ የተኛህበትን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ። 14ዘርህ እንደ ምድር አሸዋ ይበዛል፤ በምዕራብና በምሥራቅ፣ በሰሜንና በደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በአንተና በዘርህ አማካይነት ይባረካሉ። 15እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የሰጠሁህን ተስፋ እስከምፈጽምልህ ድረስ አልተውህም።”
16ያዕቆብም ከእንቅልፉ ሲነቃ፣ “በእውነት እግዚአብሔር (ያህዌ) በዚህ ስፍራ አለ፤ እኔ ግን ይህን አላወቅሁም ነበር” አለ። 17እርሱም በፍርሀት፣ “ይህ ስፍራ እንዴት የሚያስፈራ ነው! ይህስ ሌላ ሳይሆን የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ቤት መሆን አለበት፤ የሰማይ ደጅ ነው” አለ።
18ያዕቆብም በማግስቱም ማልዶ ተነሣ፣ ተንተርሶት ያደረውን ድንጋይ አንሥቶ እንደ ሐውልት አቆመው፤ በዐናቱም ላይ የወይራ ዘይት አፈሰሰበት። 19ያንን ቦታ ቤቴል#28፥19 ቤቴል ማለት የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው። ብሎ ሰየመው፤ ቀደም ሲል ግን የከተማዪቱ ስም ሎዛ ነበር።
20ከዚያም ያዕቆብ እንዲህ ሲል ተሳለ፤ “እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ከእኔ ጋር ቢሆን በምሄድበትም መንገድ ቢጠብቀኝ፣ የምበላው ምግብ፣ የምለብሰው ልብስ ቢሰጠኝ 21ወደ አባቴ ቤትም በደኅና ቢመልሰኝ፣ እግዚአብሔር አምላኬ (ያህዌ ኤሎሂም) ይሆናል፤ 22ይህ ሐውልት አድርጌ ያቆምሁት ድንጋይ፣ የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ቤት ይሆናል፤ ከምትሰጠኝም ሀብት ሁሉ፣ ከዐሥር እጅ አንዱን ለአንተ እሰጣለሁ።”

Kasalukuyang Napili:

ዘፍጥረት 28: NASV

Haylayt

Ibahagi

Kopyahin

None

Gusto mo bang ma-save ang iyong mga hinaylayt sa lahat ng iyong device? Mag-sign up o mag-sign in