1
የሉቃስ ወንጌል 14:26
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
“ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት እንኳን ሳይቀር ካልናቀ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
Karşılaştır
የሉቃስ ወንጌል 14:26 keşfedin
2
የሉቃስ ወንጌል 14:27
ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
የሉቃስ ወንጌል 14:27 keşfedin
3
የሉቃስ ወንጌል 14:11
ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል።”
የሉቃስ ወንጌል 14:11 keşfedin
4
የሉቃስ ወንጌል 14:33
እንግዲህ እንደዚሁ ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ማንም ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
የሉቃስ ወንጌል 14:33 keşfedin
5
የሉቃስ ወንጌል 14:28-30
ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ እንዳለው አስቀድሞ ተቀምጦ ወጪውን የማይቈጥር ማን ነው? ያለዚያ መሠረቱን ቢያኖር፥ ሊደመድመውም ቢያቅተው፥ ያዩት ሁሉ ‘ይህ ሰው ሊሠራ ጀምሮ መደምደም አቃተው፤’ ብለው ሊቀልዱበት ይጀምራሉ።
የሉቃስ ወንጌል 14:28-30 keşfedin
6
የሉቃስ ወንጌል 14:13-14
ነገር ግን ግብዣ ባሰናዳህ ጊዜ ድሆችንና ጉንድሾችን አንካሶችንም ዐይነ ስውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት አጸፋ የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና።”
የሉቃስ ወንጌል 14:13-14 keşfedin
7
የሉቃስ ወንጌል 14:34-35
“ጨው መልካም ነው፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ለምድርም ሆነ ለፍግ መቈለያ አይጠቅምም፤ ወደ ውጭም ይጥሉታል። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”
የሉቃስ ወንጌል 14:34-35 keşfedin
Ana Sayfa
Kutsal Kitap
Okuma Planları
Videolar