ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 17

17
ግዝ​ረት የቃል ኪዳን ምል​ክት ሆኖ መሰ​ጠቱ
1ከዚ​ህም በኋላ አብ​ራም የዘ​ጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ራም ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለው “በፊ​ትህ የሄ​ድሁ ፈጣ​ሪህ#“በፊ​ትህ የሄ​ድሁ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መል​ካም አድ​ርግ፤ ንጹ​ሕም ሁን፤ 2ቃል ኪዳ​ኔ​ንም በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል አጸ​ና​ለሁ፤ እጅ​ግም አበ​ዛ​ሃ​ለሁ።” 3አብ​ራ​ምም በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን እን​ዲህ አለው፦ 4“እነሆ፥ ቃል ኪዳ​ኔን በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል አጸ​ና​ለሁ፤ ለብዙ አሕ​ዛ​ብም አባት ትሆ​ና​ለህ። 5እን​ግ​ዲህ ስምህ አብ​ራም አይ​ባ​ልም ‘አብ​ር​ሃም’ ይባ​ላል እንጂ፤ ለብዙ አሕ​ዛብ አባት አድ​ር​ጌ​ሃ​ለ​ሁና። 6እጅ​ግም በጣም አበ​ዛ​ሃ​ለሁ፤ ሕዝ​ብም፥ ነገ​ሥ​ታ​ትም ከአ​ንተ እን​ዲ​ወጡ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ። 7ቃል ኪዳ​ኔ​ንም በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል፥ ከአ​ን​ተም በኋላ በዘ​ርህ መካ​ከል በት​ው​ል​ዳ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን አቆ​ማ​ለሁ፤ ለአ​ን​ተና ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ አም​ላክ እሆን ዘንድ። 8በው​ስ​ጥዋ የም​ት​ኖ​ር​ባ​ትን ይህ​ችን ምድር፥ የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር ሁሉ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዙ​አት ዘንድ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።”
9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “አንተ ደግሞ ቃል ኪዳ​ኔን ትጠ​ብ​ቃ​ለህ፤ አንተ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ዘርህ በት​ው​ል​ዳ​ቸው። 10በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል፥ ከአ​ን​ተም በኋላ በዘ​ርህ መካ​ከል የም​ት​ጠ​ብ​ቋት ቃል ኪዳኔ ይህች ናት፤ ከእ​ና​ንተ ወንድ ሁሉ ይገ​ረዝ። 11የሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁን ቍል​ፈት ትገ​ረ​ዛ​ላ​ችሁ፤ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ላለ​ውም ቃል ኪዳን ምል​ክት ይሆ​ናል። 12ሕፃ​ኑ​ንም በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ትገ​ር​ዙ​ታ​ላ​ችሁ፤ በቤት የተ​ወ​ለደ ወይም ከዘ​ራ​ችሁ ያይ​ደለ፥ በብ​ርም ከእ​ን​ግዳ ሰው የተ​ገዛ ወንድ ሁሉ በት​ው​ል​ዳ​ችሁ ይገ​ረዝ። 13በቤ​ት​ህም የተ​ወ​ለደ፥ በብ​ርም የተ​ገዛ ፈጽሞ ይገ​ረዝ።#በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. ብቻ። ቃል ኪዳ​ኔም በሥ​ጋ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ይሆ​ናል። 14በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን የሥ​ጋ​ውን ቍል​ፈት ያል​ተ​ገ​ረዘ፥ ያች ነፍስ ከወ​ገ​ንዋ ተለ​ይታ ትጥፋ፤ ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሳ​ለ​ችና።”
15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ሚስ​ትህ ሦራ እን​ግ​ዲህ ሦራ ተብላ አት​ጠ​ራም፤ ስምዋ ‘ሣራ’ ይሆ​ናል እንጂ። 16እባ​ር​ካ​ታ​ለ​ሁና፥ ከአ​ን​ተም ልጆ​ችን እሰ​ጣ​ታ​ለ​ሁና፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከእ​ር​ስዋ ልጆች እሰ​ጥ​ሀ​ለሁ” ይላል። አሕ​ዛ​ብና የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ከእ​ር​ስዋ ይወ​ጣሉ።”#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እባ​ር​ካ​ታ​ለሁ ከእ​ር​ስ​ዋም ልጅን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ እባ​ር​ከ​ው​ማ​ለሁ ሕዝ​ብም ይሆ​ናል የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታ​ትም ከእ​ርሱ ይወ​ጣሉ” ይላል። 17አብ​ር​ሃ​ምም በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ ሳቀም፤ በል​ቡም እን​ዲህ ብሎ አሰበ፥ “የመቶ ዓመት ሰው ስሆን በውኑ እኔ ልጅ እወ​ል​ዳ​ለ​ሁን? ዘጠና ዓመት የሆ​ና​ትም ሣራ ትወ​ል​ዳ​ለ​ችን?” 18አብ​ር​ሃ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ይህ ይስ​ማ​ኤል ብቻ በፊ​ትህ ይኖ​ር​ልኝ ዘንድ አቤቱ፥ እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ።” 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “እሺ እነሆ፥ ሚስ​ትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወ​ል​ድ​ል​ሃ​ለች፤ ስሙ​ንም ይስ​ሐቅ ብለህ ትጠ​ራ​ዋ​ለህ፤ ለእ​ር​ሱና ከእ​ርሱ በኋላ ለዘሩ አም​ላክ እሆን ዘንድ ቃል ኪዳ​ኔን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ከእ​ርሱ ጋር አቆ​ማ​ለሁ። 20ስለ ይስ​ማ​ኤ​ልም እነሆ፥ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ እጅ​ግም አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዐሥራ ሁለት አለ​ቆ​ች​ንም ይወ​ል​ዳል፤ ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ። 21ቃል ኪዳ​ኔን ግን በሚ​መ​ጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከም​ት​ወ​ል​ድ​ልህ ከይ​ስ​ሐቅ ጋር አቆ​ማ​ለሁ።”
22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንግ​ግ​ሩን ከእ​ርሱ ጋር በፈ​ጸመ ጊዜ ከአ​ብ​ር​ሃም ተለ​ይቶ ወጣ። 23አብ​ር​ሃ​ምም ልጁን ይስ​ማ​ኤ​ልን፥ በቤ​ቱም የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን ሁሉ፥ በወ​ር​ቅም የገ​ዛ​ውን ወንድ ሁሉ፥ ከቤተ ሰቡም ወን​ዶ​ቹን ሁሉ ወሰደ። የሥ​ጋ​ቸ​ው​ንም ቍል​ፈት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ለው በዚ​ያው ቀን ገረዘ። 24አብ​ር​ሃ​ምም የሥ​ጋ​ውን ቍል​ፈት በተ​ገ​ረዘ ጊዜ ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሆኖት ነበረ፤ 25ልጁ ይስ​ማ​ኤ​ልም የሥ​ጋ​ውን ቍል​ፈት በተ​ገ​ረዘ ጊዜ ዐሥራ ሦስት ዓመት ሆኖት ነበረ። 26በዚ​ያም ቀን አብ​ር​ሃም ተገ​ረዘ፤ ልጁ ይስ​ማ​ኤ​ልም። 27በቤት የተ​ወ​ለ​ዱ​ትና በብር ከእ​ን​ግ​ዶች የተ​ገ​ዙት፥ የቤቱ ወን​ዶች ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ተገ​ረዙ።

Позначайте

Поділитись

Копіювати

None

Хочете, щоб ваші позначення зберігалися на всіх ваших пристроях? Зареєструйтеся або увійдіть