ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 18

18
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃም እንደ ተገ​ለጠ
1በቀ​ት​ርም ጊዜ አብ​ር​ሃም በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ተቀ​ምጦ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ምሬ ዛፍ ሥር ተገ​ለ​ጠ​ለት። 2ዐይ​ኑ​ንም በአ​ነሣ ጊዜ እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያ​ቸ​ውም ጊዜ ሊቀ​በ​ላ​ቸው ከድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ተነ​ሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድ​ርም ሰገደ፤ 3እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ በፊ​ት​ህስ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ ባሪ​ያ​ህን አት​ለ​ፈው፤ 4ውኃ እና​ም​ጣ​ላ​ችሁ፤ እግ​ራ​ች​ሁ​ንም እን​ጠ​ባ​ችሁ። 5ከዛ​ፉም ሥር ዕረፉ፤ እን​ጀ​ራም እና​ም​ጣ​ላ​ች​ሁና ብሉ፤ ከዚ​ያም በባ​ሪ​ያ​ችሁ ዘንድ ከአ​ረ​ፋ​ችሁ በኋላ፥ ወደ ዐሰ​ባ​ች​ሁት ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “እን​ዳ​ልህ እን​ዲሁ አድ​ርግ” አሉት። 6አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ድን​ኳን ወደ ሚስቱ ወደ ሣራ ፈጥኖ ገባና፥ “ሦስት መስ​ፈ​ሪያ የተ​ሰ​ለቀ ዱቄት ፈጥ​ነሽ ለውሺ፤ እን​ጎ​ቻም አድ​ርጊ” አላት። 7አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፤ እጅግ የሰ​ባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብ​ላ​ቴ​ናው ሰጠው፤ ያዘ​ጋ​ጅም ዘንድ ተቻ​ኮለ። 8እር​ጎና መዓር፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ቅቤና ወተት” ይላል። ያን ያዘ​ጋ​ጀ​ው​ንም ጥጃ አመጣ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም አቀ​ረ​በው፤ እር​ሱም ከዛፉ በታች በፊ​ታ​ቸው ቆሞ ያሳ​ል​ፍ​ላ​ቸው ነበር፤ እነ​ር​ሱም በሉ።
ለአ​ብ​ር​ሃም ወንድ ልጅ እን​ደ​ሚ​ወ​ለ​ድ​ለት የተ​ሰ​ጠው ተስፋ
9እር​ሱም፥ “ሚስ​ትህ ሣራ ወዴት ናት?” አለው። እር​ሱም፥ “በድ​ን​ኳኑ ውስጥ ናት” አለው። 10እር​ሱም፥ “የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ወደ አንተ ተመ​ልሼ እመ​ጣ​ለሁ፤ ሚስ​ትህ ሣራም ልጅን ታገ​ኛ​ለች” አለ። 11ሣራም በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ በስ​ተ​ኋ​ላው ቆማ ሳለች ይህን ሰማች። አብ​ር​ሃ​ምና ሣራም በዕ​ድ​ሜ​ያ​ቸው ሸም​ግ​ለው ፈጽ​መው አር​ጅ​ተው ነበር፤ በሴ​ቶች የሚ​ሆ​ነ​ውም ልማድ ከሣራ ተቋ​ርጦ ነበር። 12ሣራም ለብ​ቻዋ በል​ብዋ እን​ዲህ ስትል ሳቀች፥ “እስከ ዛሬ ገና ነኝን? ጌታ​ዬም ፈጽሞ ሽም​ግ​ሎ​አል።” 13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ሣራን ለብ​ቻዋ በል​ብዋ ምን አሳ​ቃት? እስከ ዛሬ ገና ነኝን? በእ​ው​ነ​ትስ እወ​ል​ዳ​ለ​ሁን? ጌታ​ዬም አር​ጅ​ት​ዋል#“እስከ ዛሬ ገና ነኝን ጌታ​ዬም አር​ጅ​ት​ዋል” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። እነሆ፥ እኔም አር​ጅ​ቻ​ለሁ ብላ​ለ​ችና። 14በውኑ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሳ​ነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገ​ኛ​ለች።” 15ሣራም ስለ ፈራች “አል​ሳ​ቅ​ሁም” ብላ ካደች። እር​ሱም፥ “አይ​ደ​ለም፥ ሳቅሽ እንጂ” አላት።
አብ​ር​ሃም ለሰ​ዶም እንደ ማለደ
16እነ​ዚ​ያም ሰዎች ከዚያ ተነ​ሥ​ተው ወደ ሰዶ​ምና ወደ ገሞራ#“ገሞራ” በዕብ. የለም። አቀኑ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ሊሸ​ኛ​ቸው አብ​ሮ​አ​ቸው ሄደ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ተመ​ልሶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆመ።#“አብ​ር​ሃ​ምም ተመ​ልሶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆመ” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “እኔ የማ​ደ​ር​ገ​ውን ከወ​ዳጄ አብ​ር​ሃም አል​ሰ​ው​ርም፤ 18አብ​ር​ሃም በእ​ው​ነት ታላ​ቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆ​ና​ልና፤ የም​ድር ሕዝ​ቦ​ችም ሁሉ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካ​ሉና። 19ጽድ​ቅ​ንና ፍር​ድን በማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ ልጆ​ቹ​ንና ቤቱን ያዝ​ዛ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ለው አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ያደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ ነው።” 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ር​ሃም አለው፥ “የሰ​ዶ​ምና የገ​ሞራ ጩኸት በእኔ ዘንድ በዛ፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም እጅግ ከበ​ደች፤ 21እን​ግ​ዲ​ህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸቷ ይፈ​ጽ​ሙ​አት እንደ ሆነ አይ ዘንድ እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ እን​ዲ​ሁም ባይ​ሆን አው​ቃ​ለሁ።”
22ሰዎ​ቹም ከዚያ በተ​መ​ለሱ ጊዜ ወደ ሰዶም መጡ፤ አብ​ር​ሃም ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር። 23አብ​ር​ሃ​ምም ቀረበ፤ አለም፥ “አቤቱ፥ ጻድ​ቃ​ንን ከኃ​ጥ​ኣን ጋር አታ​ጥፋ፤ ጻድቁ እንደ ኃጥኡ አይ​ሁን። 24አምሳ ጻድ​ቃን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠ​ፋ​ለ​ህን? ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንስ በእ​ር​ስዋ ስለ​ሚ​ገኙ አምሳ ጻድ​ቃን አት​ም​ር​ምን? 25አቤቱ ይህ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም፤ ይህን ነገር አታ​ድ​ርግ፤ ጻድ​ቃ​ንን ከኃ​ጥ​ኣን ጋር አታ​ጥፋ፤ ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ገዛ ይህን ፍርድ ታደ​ርግ ዘንድ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም።” 26እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “በሰ​ዶም ከተማ ውስጥ አምሳ ጻድ​ቃን ባገኝ ከተ​ማ​ውን ሁሉ ስለ እነ​ርሱ አድ​ና​ለሁ።” 27አብ​ር​ሃ​ምም መለሰ፤ አለም፥ “እኔ አፈ​ርና አመድ ስሆን ከጌ​ታዬ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር እና​ገር ዘንድ አሁን ጀመ​ርሁ፤ 28ከእ​ነ​ዚያ አምሳ ጻድ​ቃን አም​ስት ቢጐ​ድሉ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሁሉ በጐ​ደ​ሉት በአ​ም​ስቱ ምክ​ን​ያት ታጠ​ፋ​ለ​ህን?” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ከዚያ አርባ አም​ስት ባገኝ ስለ እነ​ርሱ አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው። 29አብ​ር​ሃ​ምም አለው፥ “ከዚያ አርባ ቢገ​ኙሳ?” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ለአ​ር​ባው ስል አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው። 30አብ​ር​ሃ​ምም እን​ደ​ገና ነገ​ሩን ደገመ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከዚያ ሠላሳ ቢገ​ኙሳ?” እር​ሱም፥ “ስለ ሠላ​ሳው አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው። 31ደግ​ሞም፥ “እነሆ፥ ከጌ​ታዬ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር እነ​ጋ​ገር ዘንድ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን ካገ​ኘሁ ከዚያ ሃያ ቢገ​ኙሳ?” አለው። እር​ሱም፥ “ስለ ሃያው አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው። 32አብ​ር​ሃ​ምም አለው፥ “አቤቱ እን​ደ​ገና እና​ገር ዘንድ ፍቀ​ድ​ልኝ፤ ከዚያ ዐሥር ቢገ​ኙሳ?” እር​ሱም፥ “ስለ ዐሥሩ አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው።#ምዕ. 18 ቍ. 30 እና 32 ላይ በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. “ጌታዬ ሆይ እንደ ገና አንድ ጊዜ ብና​ገር በእኔ ላይ አን​ዳች ነገር ይሆ​ና​ልን?” ይላል። 33እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ብ​ር​ሃም ጋር ንግ​ግ​ሩን በጨ​ረሰ ጊዜ ሄደ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ።

Позначайте

Поділитись

Копіювати

None

Хочете, щоб ваші позначення зберігалися на всіх ваших пристроях? Зареєструйтеся або увійдіть