ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 20

20
አብ​ር​ሃ​ምና አቤ​ሜ​ሌክ
1አብ​ር​ሃ​ምም ከዚያ ተነ​ሥቶ ወደ አዜብ ምድር አቅ​ጣጫ ሄደ፤ በቃ​ዴ​ስና በሱር መካ​ከ​ልም ኖረ፤ በጌ​ራ​ራም በእ​ን​ግ​ድ​ነት ተቀ​መጠ። 2አብ​ር​ሃ​ምም ሚስ​ቱን ሣራን “እኅቴ ናት” አላ​ቸው፤ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ሰዎች ስለ እር​ስዋ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉት “ሚስቴ” ናት ማለ​ትን ፈር​ቶ​አ​ልና፤ የጌ​ራራ ንጉሥ አቤ​ሜ​ሌ​ክም ላከና ሣራን ወሰ​ዳት። 3በዚ​ያች ሌሊ​ትም አቤ​ሜ​ሌክ ተኝቶ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ልም ወደ እርሱ መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰ​ድ​ሃት ሴት ትሞ​ታ​ለህ፤ እር​ስዋ ባለ ባል ናትና።” 4አቤ​ሜ​ሌክ ግን አል​ቀ​ረ​ባ​ትም ነበር፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክም እን​ዲህ አለ፥ “አቤቱ ያላ​ወ​ቀ​ውን ሕዝብ በእ​ው​ነት ታጠ​ፋ​ለ​ህን? 5እኅቴ ናት ያለኝ እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን? እር​ስዋ ደግሞ ራስዋ ወን​ድሜ ነው አለች፤ በልቤ ቅን​ነ​ትና በእጄ ንጹ​ሕ​ነት ይህን አደ​ረ​ግ​ሁት።” 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም አለው፥ “ይህን በል​ብህ ቅን​ነት እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ እኔ ዐወ​ቅሁ፤ እኔም ደግሞ በፊቴ ኀጢ​አ​ትን እን​ዳ​ት​ሠራ ጠበ​ቅ​ሁህ፤ ስለ​ዚ​ህም ትቀ​ር​ባት ዘንድ አል​ተ​ው​ሁ​ህም። 7አሁ​ንም የሰ​ው​የ​ውን ሚስት መልስ፤ ነቢይ ነውና፥ ስለ አን​ተም ይጸ​ል​ያል፤ ትድ​ና​ለ​ህም። ባት​መ​ል​ሳት ግን አንተ እን​ድ​ት​ሞት፥ ለአ​ንተ የሆ​ነ​ውም ሁሉ እን​ዲ​ሞት በር​ግጥ ዕወቅ።” 8አቤ​ሜ​ሌ​ክም በጥ​ዋት ተነሣ፤ ብላ​ቴ​ኖ​ቹ​ንም ሁሉ ጠራ፤ ይህ​ንም ነገር ሁሉ በጆ​ሮ​አ​ቸው ተና​ገረ፤ ቤተ ሰዎ​ቹም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጅግ ፈሩ። 9አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ምንስ ክፉ ሠራ​ሁ​ብህ? በእ​ኔና በመ​ን​ግ​ሥቴ ላይ ትልቅ ኀጢ​አት አው​ር​ደ​ሃ​ልና፤ ማንም የማ​ያ​ደ​ር​ገው የማ​ይ​ገባ ሥራ በእኔ ሠራ​ህ​ብኝ።” 10አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ይህን ነገር ማድ​ረ​ግህ ምን አይ​ተህ ነው?” 11አብ​ር​ሃ​ምም አለ፥ “ምን​አ​ል​ባት በዚህ ስፍራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ስለ​ሌለ በሚ​ስቴ ምክ​ን​ያት ይገ​ድ​ሉ​ኛል ብዬ ነው። 12እር​ስ​ዋም ደግሞ በእ​ናቴ ወገን አይ​ደ​ለ​ችም እንጂ በእ​ው​ነት በአ​ባቴ ወገን እኅቴ ናት፤ ለእ​ኔም ሚስት ሆነች። 13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ባቴ ቤት ባወ​ጣኝ ጊዜ አል​ኋት፥ ‘ይህን ጽድቅ አድ​ር​ጊ​ልኝ፤ በገ​ባ​ን​በት ሀገር ሁሉ ወን​ድሜ ነው በዪ።’ ” 14አቤ​ሜ​ሌ​ክም አንድ ሺህ ምዝ​ምዝ ብርን#“አንድ ሺህ ምዝ​ምዝ ብርን” የሚ​ለው በዕብ. የለም። በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችን አመጣ፤ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምም ሰጠው፤ ሚስ​ቱን ሣራ​ንም መለ​ሰ​ለት። 15አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “እነሆ፥ ምድሬ በፊ​ትህ ናት፤ በወ​ደ​ድ​ኸው ተቀ​መጥ።” 16ሣራ​ንም አላት “እነሆ፥ ለወ​ን​ድ​ምሽ አንድ ሺህ ምዝ​ምዝ ብር ሰጠ​ሁት፤ ይህም ለፊ​ትሽ ክብር ይሁ​ንሽ፤ በሁ​ሉም እው​ነ​ትን ተና​ገ​ራት።” 17አብ​ር​ሃ​ምም ወደ እግ​ዚ​ዘ​ብ​ሔር ጸለየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ ሚስ​ቱ​ንም፥ ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም፥ በቤቱ ውስጥ ያሉ ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ፈወ​ሳ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ወለዱ፤ 18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ብ​ር​ሃም ሚስት በሣራ ምክ​ን​ያት በአ​ቤ​ሜ​ሌክ ቤት ማኅ​ፀ​ኖ​ችን ሁሉ በፍ​ጹም ዘግቶ ነበ​ርና።

Позначайте

Поділитись

Копіювати

None

Хочете, щоб ваші позначення зберігалися на всіх ваших пристроях? Зареєструйтеся або увійдіть