1
ዳንኤል 5:23
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ይልቁንም በሰማይ አምላክ ላይ በመታበይ፣ ራስህን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ የመቅደሱን መጠጫዎች አስመጣህ፤ አንተና መኳንንትህ፣ ሚስቶችህና ቍባቶችህም የወይን ጠጅ ጠጣችሁባቸው፤ ማየት፣ መስማት፣ ማስተዋልም የማይችሉትን የብርና የወርቅ፣ የናስና የብረት፣ የዕንጨትና የድንጋይ አማልክትን አመሰገንህ። ሕይወትህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ ግን አላከበርህም።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ዳንኤል 5:25-28
“የተጻፈውም ጽሕፈት፣ ‘ማኔ፣ ማኔ፣ ቴቄል፣ ፋሬስ’ ይላል። “የቃሉም ትርጕም ይህ ነው፤ “ ማኔ ማለት አምላክ የመንግሥትህን ዘመን ቈጠረው፤ ወደ ፍጻሜም አደረሰው ማለት ነው። “ ቴቄል ማለት በሚዛን ተመዘንህ፤ ቀለህም ተገኘህ፣ ማለት ነው። “ ፋሬስ ማለት መንግሥትህ ተከፈለ፣ ለሜዶናውያንና ለፋርስ ሰዎች ተሰጠ ማለት ነው።”
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች