ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና ርግማንን በፊትህ እንዳስቀመጥሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራብሃለሁ። እንግዲህ አንተና ልጆችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ፤ ይኸውም አምላክህን እግዚአብሔርን እንድትወድድ፣ ቃሉን እንድታደምጥና ከርሱ ጋራ እንድትጣበቅ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕይወትህ ነው፤ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ ሊሰጣቸው በማለላቸው ምድር ረዥም ዕድሜ ይሰጥሃል።