1
ዘፀአት 7:1
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ልብ በል፤ እኔ አንተን ለፈርዖን እንደ አምላክ አድርጌሃለሁ፤ ወንድምህ አሮንም ያንተ ነቢይ ይሆናል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ዘፀአት 7:3-4
እኔ ግን የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ፤ ታምራዊ ምልክቶችንና ድንቆችን በግብጽ ላይ በብዛት ባደርግም እንኳ፣ አይሰማችሁም። ከዚያም እጄን በግብጽ ላይ አደርጋለሁ፤ በኀያል ፍርድም ሰራዊቴን፣ ሕዝቤን እስራኤላውያንን አወጣለሁ።
3
ዘፀአት 7:5
እጄን በግብጽ ላይ ስዘረጋና እስራኤላውያንንም ከዚያ ሳወጣ፣ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”
4
ዘፀአት 7:11-12
ከዚያም ፈርዖን ጠቢባኑንና መተተኞቹን ጠራ፤ የግብጽ አስማተኞችም በድብቅ ጥበባቸው ያንኑ አደረጉ፤ እያንዳንዱ የያዛትን በትር ጣለ፤ እባብም ሆነች። ነገር ግን የአሮን በትር የእነርሱን በትሮች ዋጠች።
5
ዘፀአት 7:17
እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ “እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እይ! በዚህች በእጄ በያዝኋት በትር የአባይን ውሃ እመታለሁ፤ ወደ ደምም ይለወጣል።
6
ዘፀአት 7:9-10
“ፈርዖን፣ ‘ታምር አሳዩኝ’ ባላችሁ ጊዜ፣ አሮንን እንዲህ በለው፤ ‘በትርህን ውሰድና በፈርዖን ፊት ጣላት፤’ ከዚያም እባብ ትሆናለች።” ስለዚህ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ። አሮን በትሩን በፈርዖንና በሹማምቱ ፊት ጣላት፤ እባብም ሆነች።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች