1
ዘፍጥረት 27:28-29
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እግዚአብሔር የሰማይን ጠል፣ የምድርንም በረከት፣ የተትረፈረፈ እህልና የወይን ጠጅ ይስጥህ። መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችም ተደፍተው እጅ ይንሡህ፤ የወንድሞችህ ጌታ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ተደፍተው እጅ ይንሡህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚባርኩህ የተባረኩ ይሁኑ።”
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ዘፍጥረት 27:36
ዔሳውም፣ “ይህ ሰው ያዕቆብ መባሉ ትክክል አይደለምን? እኔን ሲያታልለኝ ይህ ሁለተኛ ጊዜው ነው፤ መጀመሪያ ብኵርናዬን ወሰደብኝ፤ አሁን ደግሞ ምርቃቴን ቀማኝ” አለ። ቀጥሎም፣ “ታዲያ ለእኔ ያስቀረኸው ምንም ምርቃት የለም?” ብሎ ጠየቀ።
3
ዘፍጥረት 27:39-40
አባቱ ይሥሐቅም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “መኖሪያህ ከምድር በረከት፣ ከላይም ከሰማይ ጠል የራቀ ይሆናል፤ በሰይፍ ትኖራለህ፤ የወንድምህም አገልጋይ ትሆናለህ። አምርረህ በተነሣህ ጊዜ ግን፣ ቀንበሩን ከጫንቃህ ላይ፣ ወዲያ ትጥላለህ።”
4
ዘፍጥረት 27:38
ዔሳውም አባቱን፣ “አባቴ ሆይ፤ ምርቃትህ ይህችው ብቻ ናትን? እባክህ አባቴ፣ እኔንም መርቀኝ” አለው፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ።
Home
Bible
Plans
Videos