1
መዝሙር 112:7
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ክፉ ወሬ አያሸብረውም፤ ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መዝሙር 112:1-2
ሃሌ ሉያ። ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ በትእዛዙም እጅግ ደስ የሚሰኝ፤ ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይሆናል፤ የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።
3
መዝሙር 112:8
ልቡ የጸና ነው፤ አይፈራምም፤ በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።
4
መዝሙር 112:4
ቸር፣ ርኅሩኅና ጻድቅ እንደ መሆኑ፣ ለቅን ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል።
5
መዝሙር 112:5
ለጋስና ያለ ማንገራገር የሚያበድር፣ ሥራውንም በትክክል የሚያከናውን ሰው መልካም ይሆንለታል።
6
መዝሙር 112:6
ለዘላለም ከስፍራው አይናወጥምና፤ ጻድቅ ሰው ሲታወስ ይኖራል።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች