1
1 ወደ ጢሞቴዎስ 6:12
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
የእምነትን መልካም ጦርነት ተዋጋ፤ አንተ ወደ እርሱ በተጠራህ ጊዜ በብዙ ምስክሮች ፊት ትክክለኛ ምስክርነትን የሰጠኸውን ዘለዓለማዊውን ሕይወት ያዝ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
1 ወደ ጢሞቴዎስ 6:10
ይህም የሚሆነው የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ምንጭ ስለ ሆነ ነው።
3
1 ወደ ጢሞቴዎስ 6:6
“ያለኝ ይበቃኛል” ለሚል ሰው እግዚአብሔርን ማምለክ ትልቅ ጥቅም ያስገኝለታል። መንፈሳዊነትን ስለሚያተርፍበት ሃይማኖት የሀብት ምንጭ ነው።
4
1 ወደ ጢሞቴዎስ 6:7
ወደዚህ ዓለም ምንም ይዘን አልመጣንም፤ ከዚህም ዓለም ይዘነው የምንሄድ ምንም ነገር የለም።
5
1 ወደ ጢሞቴዎስ 6:17
የዚህ ዓለም ሀብታሞች እንዳይታበዩ ወይም ተስፋቸውን አስተማማኝ ባልሆነ ሀብት ላይ እንዳያደርጉ እዘዛቸው፤ እንዲሁም ተስፋቸው እኛን ደስ እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን እዘዛቸው።
6
1 ወደ ጢሞቴዎስ 6:9
ሀብታሞች ለመሆን የሚፈልጉ ግን በፈተና ይወድቃሉ፤ ሰዎችን በሚያበላሽና በሚያጠፋ ከንቱና አደገኛ በሆነ በብዙ ምኞት ወጥመድ ይያዛሉ።
7
1 ወደ ጢሞቴዎስ 6:18-19
ደግሞም መልካም ሥራ እንዲሠሩ፥ በመልካም ሥራ ሀብታሞች እንዲሆኑ፥ ለመለገሥና ያላቸውንም ለማካፈል ዝግጁዎች እንዲሆኑ እዘዛቸው። በዚህ ዐይነት እውነተኛውን ሕይወት ለማግኘት መሠረቱ ጽኑ የሆነውን ሀብት በሚመጣው ዘመን ለራሳቸው ያከማቻሉ።
Home
Bible
Plans
Videos