1
ትንቢተ ሕዝቅኤል 33:11
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ ኃጢአተኛ ሰው፥ ኃጢአት መሥራቱን ትቶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ በኃጢአቱ እንዲሞት አልፈቅድም፤ ስለዚህ እስራኤል ሆይ! ክፉ ሥራችሁን ተዉ፤ መሞትን ለምን ትፈልጋላችሁ? ብለህ ንገራቸው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ሕዝቅኤል 33:7
“አሁንም የሰው ልጅ ሆይ! እነሆ፥ እኔ አንተን ለእስራኤል ሕዝብ ጠባቂ አድርጌሃለሁ፤ እኔ የምሰጥህን ማስጠንቀቂያ ሁሉ ለእነርሱ ማስተላለፍ አለብህ፤
3
ትንቢተ ሕዝቅኤል 33:9
ኃጢአተኛውን ሰው ከክፉ ሥራው እንዲመለስ ካስጠነቀቅኸው በኋላ፥ ከክፉ ሥራው ሳይመለስ በኃጢአቱ ጸንቶ ቢሞት ግን፥ አንተ ራስህን ከኀላፊነት ነጻ ታደርጋለህ።”
4
ትንቢተ ሕዝቅኤል 33:6
ነገር ግን ጠባቂው ጠላት ሲመጣ እያየ ከአደጋ ማስጠንቀቂያውን ድምፅ ሳያሰማ ቢቀር፥ ጠላት መጥቶ ከእነዚያ መካከል አንዱን ቢገድል ያ ሰው የሞተው በኀጢአቱ ነው፤ እኔ ግን ስለ እርሱ ለደሙ ኀላፊ አድርጌ የምጠይቀው ጠባቂውን ነው።’
5
ትንቢተ ሕዝቅኤል 33:5
ማስጠንቀቂያውን ባለማጤኑ ለሞት ያበቃው የራሱ ስሕተት ነው፤ ማስጠንቀቂያውን ቢያጤንማ ኖሮ ከጥፋት ባመለጠ ነበር፤
Home
Bible
Plans
Videos