1
የማቴዎስ ወንጌል 27:46
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን ኢየሱስ፦ “ኤሎሄ! ኤሎሄ! ላማ ሰበቅታኒ?” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም “አምላኬ! አምላኬ! ለምን ተውከኝ?” ማለት ነው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
የማቴዎስ ወንጌል 27:51-52
በዚያን ጊዜ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀዶ ከሁለት ተከፈለ፤ ምድርም ተናወጠች፤ አለቶችም ተሰነጠቁ፤ መቃብሮችም ተከፍተው ሞተው ከነበሩት ቅዱሳን ሰዎች ብዙዎች ከሞት ተነሡ።
3
የማቴዎስ ወንጌል 27:50
ኢየሱስ እንደገና በታላቅ ድምፅ ጮኸና ነፍሱን ሰጠ።
4
የማቴዎስ ወንጌል 27:54
የመቶ አለቃውና ከእርሱም ጋር ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት የምድርን መናወጥና የሆነውንም ነገር ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው “በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ!” አሉ።
5
የማቴዎስ ወንጌል 27:45
ከስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ጨለማ ሆነ።
6
የማቴዎስ ወንጌል 27:22-23
ጲላጦስም “ታዲያ፥ መሲሕ የተባለውን ኢየሱስን ምን ላድርገው?” አላቸው። ሁሉም “ይሰቀል!” ሲሉ መለሱ። ገዢውም ለምን? “እርሱ ያደረገው በደል ምንድን ነው?” አላቸው። እነርሱ ግን “ይሰቀል!” እያሉ አብዝተው ጮኹ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች