1
መጽሐፈ ምሳሌ 2:6
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ጥበብን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ ዕውቀትና ማስተዋልም የሚገኙት ከእርሱ ዘንድ ነው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 2:1-5
ልጄ ሆይ! የማስተምርህን ተቀበል፤ ትእዛዞቼንም በልብህ አኑር። የጥበብን ቃል አድምጥ፤ በጥንቃቄም አስተውለው። ማስተዋልን ጥራ፤ ለዕውቀትም ድምፅህን ከፍ አድርግ። ብር ወይም የተሰወረ ሀብት ለማግኘት ጥረት የምታደርገውን ያኽል ተግተህ ጥበብን ፈልጋት። ይህን ሁሉ ብታደርግ እግዚአብሔርን መፍራት ምን እንደ ሆነ ታውቃለህ፤ የአምላክንም ዕውቀት ታገኛለህ።
3
መጽሐፈ ምሳሌ 2:7-8
እርሱ ለቀጥተኞች መልካም ጥበብን ይሰጣል፤ በተግባራቸው ነቀፋ ለሌለባቸው ጋሻቸው ነው። የፍትሕን ሂደት ይከታተላል፤ በታማኝነት የሚያገለግሉትንም ይጠብቃል።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 2:21-22
በዚህች ምድር መኖር የሚችሉት ልበ ቅኖችና ደጋግ ሰዎች ናቸው። ክፉ ሰዎችን ግን እግዚአብሔር ከምድር ላይ በሞት ይነጥቃቸዋል፤ ከዳተኞችንም እንደ አረም ነቃቅሎ ያጠፋቸዋል።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 2:16-17
እንግዲህ እኔ የምልህን ብትሰማ በልዝብ አነጋገር ከምታጠምድ ከአመንዝራ ሴት ማምለጥ ትችላለህ። እንደዚህ ያለችው ሴት ለልጅነት ባልዋ ያላትን ታማኝነት የምታጓድልና በእግዚአብሔር ፊት የገባችውንም ቃል ኪዳን የምትዘነጋ ናት።
Home
Bible
Plans
Videos