1
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:3-4
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይባረክ። እኛ በእግዚአብሔር በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ያሉትን ሁሉ ማጽናናት እንድንችል፥ እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:5
የክርስቶስ ሥቃይ ስለ እኛ እንደ መብዛቱ፥ መጽናናታችንም በክርስቶስ በኩል ይበዛልናል።
3
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:9
በእርግጥም፥ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፥ የሞት ፍርድ እንደተላለፈብን በውስጣችን ተሰምቶን ነበር።
4
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:21-22
ነገር ግን በክርስቶስ ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፤ ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።
5
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:6
መከራ ብንቀበል፥ ስለ መጽናናታችሁና ስለ መዳናችሁ ነው፤ ብንጽናናም፥ እኛ የተቀበልነውን መከራ በመቀበል እናንተም በትዕግሥት መታገስ በመቻላችሁ፥ ስለ መጽናናታችሁ ነው።
Home
Bible
Plans
Videos