1
የማቴዎስ ወንጌል 22:37-39
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
እርሱም እንዲህ አለው “‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ።’ ታላቂቱና የመጀመሪያይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርሷም ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤’ የምትለው ናት።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
የማቴዎስ ወንጌል 22:40
በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕግና ነቢያት ሁሉ ተንጠልጥለዋል።”
3
የማቴዎስ ወንጌል 22:14
የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።”
4
የማቴዎስ ወንጌል 22:30
በሙታን ትንሣኤ ጊዜ እንደ መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም ወይም አይጋቡም።
5
የማቴዎስ ወንጌል 22:19-21
ለግብር የሚከፈለውን ብር አሳዩኝ።” እነርሱም ዲናር አመጡለት። እርሱም “ይህ መልክና ጽሑፉ የማን ነው?” አላቸው። እነርሱም “የቄሣር ነው” አሉት። እርሱም “እንግዲያውስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ” አላቸው።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች