1
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:18
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
“ኑና እንዋቀስ” ይላል እግዚአብሔር፤ ኀጢአታችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነጻዋለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠራዋለሁ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:19
እሽ ብትሉና ብትሰሙኝ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:17
መልካም መሥራትን ተማሩ፤ ፍርድን ፈልጉ፤ የተገፋውን አድኑ፤ ለድሃአደጉ ፍረዱለት፤ ስለ መበለቲቱም ተሙአገቱ።”
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:20
እንቢ ብትሉና ባትሰሙኝ ግን ሰይፍ ትበላችኋለች፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:16
ታጠቡ፤ ንጹሓንም ሁኑ፤ የሰውነታችሁን ክፋት ከዐይኖች ፊት አስወግዱ፤ ክፉ ማድረግንም ተዉ፤
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:15
እጃችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ፥ ዐይኖችን ከእናንተ እመልሳለሁ፤ ምህላንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደምን ተሞልተዋልና።
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:13
መልካሙን የስንዴ ዱቄት ብታመጡ እንኳ ከንቱ ነው፤ ዕጣናችሁ በእኔ ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ መባቻዎቻችሁንና ሰንበቶቻችሁን፥ ታላቋን፥ ቀናችሁን፥ ጾማችሁንና ሥራ መፍታታችሁን አልወድም።
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:3
በሬ ገዢውን አህያም የጌታውን ጋጥ ዐወቀ፤ እስራኤል ግን አላወቁኝም፤ ሕዝቤም አላስተዋሉኝም።”
9
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:14
መባቻችሁንና በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ አስጸያፊ ሆናችሁብኛል፤ ኀጢአታችሁንም ይቅር አልልም።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች