እነሆ፥ ለጠብና ለክርክር ትጾማላችሁ፤ ድሃውንም በጡጫ ትማታላችሁ፤ በምትጮኹበት ጊዜ ድምፃችሁ እንዲሰማ ለእኔ ትጾማላችሁን? ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም። እኔ ይህን ጾም የመረጥሁ አይደለሁም፤ እንደዚችም ባለች ቀን ሰው ራሱን ቢያሳዝን፥ አንገቱንም እንደ ቀለበት ቢያቀጥን፥ ማቅ ለብሶ በአመድ ላይ ቢተኛም፥ ይህ ጾም በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠ አይደለም።