1
መጽሐፈ መሳፍንት 16:20
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ደሊላም፥ “ሶምሶን ሆይ! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ከእንቅልፉም ነቅቶ፥ “እወጣለሁ፤ እንደ ወትሮውም ጊዜ አደርጋለሁ፤ አጠፋቸዋለሁም” አለ። ነገር ግን እግዚአብሔር ከእርሱ እንደ ተለየው አላወቀም።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መሳፍንት 16:28
ሶምሶንም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እንዲህም አለ፥ “አቤቱ ጌታዬ ሆይ! አስበኝ፤ ጌታዬ ሆይ! አንድ ጊዜ አበርታኝ፤ እንግዲህ ስለ ሁለቱ ዐይኖቼ ፋንታ ከፍልስጥኤማውያን አንዲት በቀልን እበቀላለሁ።”
3
መጽሐፈ መሳፍንት 16:17
እርሱም፥ “ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ ለእግዚአብሔር ናዝራዊ ነኝና ራሴን ምላጭ አልነካኝም፤ የራሴንም ጠጕር ብላጭ ኀይሌ ከእኔ ይነሣል፤ እደክማለሁም፤ እንደ ሌላም ሰው ሁሉ እሆናለሁ” ብሎ የልቡን ሁሉ ነገራት።
4
መጽሐፈ መሳፍንት 16:16
ከዚህም በኋላ ሌሊቱን ሁሉ በነገር በዘበዘበችውና በአደከመችው ጊዜ፥ ልሙት እስኪል ድረስ ተበሳጨ።
5
መጽሐፈ መሳፍንት 16:30
ሶምሶንም፥ “ከፍልስጥኤማውያን ጋር ነፍሴ ትውጣ” አለ፤ ተጎንብሶም ምሰሶዎቹን በሙሉ ኀይሉ ገፋቸው፤ ቤቱም በውስጡ በነበሩት በመሳፍንቱ፥ በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፤ በሞቱም የገደላቸው ሙታን በሕይወቱ ሳለ ከገደላቸው በዙ።
Home
Bible
Plans
Videos