1
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 6:2
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፥ “እነሆ፥ ኢያሪኮንና ንጉሥዋን ጽኑዓን፥ ኀያላንዋንም በእጅህ ሰጥቼአለሁ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 6:5
ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ፥ የመለከቱን ድምፅ ስትሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከተማዪቱም ቅጥር ይወድቃል፤ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ ፊት ለፊት እየሮጠ ይገባባታል።”
3
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 6:3
አንተም ተዋጊዎችን ሁሉ በዙሪያው አሰልፋቸው። ተዋጊዎቻችሁም ሁሉ በከተማዪቱ ዙሪያ አንድ ጊዜ ይዙሩ፤ እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ።
4
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 6:4
ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይያዙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማዪቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፤ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ።
5
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 6:1
ኢያሪኮም በግንብ ታጥራ ተዘግታ ነበር፤ ወደ እርስዋ የሚገባ፥ ከእርስዋም የሚወጣ አልነበረም።
6
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 6:16
እንዲህም ሆነ፤ ከተማዪቱን ሰባት ጊዜ በዞሩና ካህናቱ ቀንደ መለከቱን በነፉ ጊዜ፤ ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች አለ፥ “እግዚአብሔር ከተማዪቱን ሰጥቶአችኋልና ጩኹ።
7
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 6:17
ከተማዪቱም በእርስዋም ያለው ሁሉ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር እርም ይሆናሉ፤ የላክናቸውን መልእክተኞች ስለ ሸሸገች ዘማዊቱ ረዓብ፥ ከእርስዋም ጋር በቤቷ ውስጥ ያሉ ሁሉ ብቻ በሕይወት ይኖራሉ።
Home
Bible
Plans
Videos