እግዚአብሔር ግን አዲስ ነገር ቢፈጥር፥ ምድርም አፍዋን ከፍታ እነርሱን፥ ቤታቸውን፥ ድንኳናቸውን፥ ለእነርሱም ያለውን ሁሉ ብትውጣቸው፥ በሕይወታቸውም ወደ ሲኦል ቢወርዱ፥ ያንጊዜ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን እንደ አስቈጡ ታውቃላቸሁ።”
እንዲህም ሆነ፤ ይህን ቃል ሁሉ መናገር በፈጸመ ጊዜ ከበታቻቸው ያለችው መሬት ተሰነጠቀች፤ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ እነርሱን፥ ቤተ ሰቦቻቸውንም፥ ለቆሬም የነበሩትን ሰዎች ሁሉ፥ ከብቶቻቸውንም ሁሉ ዋጠቻቸው።