ዘፀአት 39
39
የካህናት አልባሳት
1ለመቅደሱ አገልግሎት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ የተፈተሉ ልብሶችን ሠሩ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለአሮን የተቀደሱ ልብሶችን ሠሩ።
ኤፉድ
39፥2-7 ተጓ ምብ – ዘፀ 28፥6-14
2ኤፉዱን ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ በቀጭኑ ከተፈተለ ሐር ሠሩት#39፥2 በዚህ እንዲሁም በቍጥር 7፣ 8 እና 22 ላይ ሥራ።። 3ጥበበኛ ባለሙያ እንደሚሠራው በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በቀጭን በፍታ ይሠራ ዘንድ ወርቁን በሥሡ ቀጥቅጠው እንደ ክር ቈራረጡት። 4ለኤፉዱ ከሁለቱ ጐኖቹ ጋራ ተያይዘው ያሉትን የትከሻ ንጣዮችን ሠሩ፤ ይኸውም ማያያዝ እንዲቻል ነው። 5በጥበብ የተፈተለው መታጠቂያ በተመሳሳይ መልክ ሆኖ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው፣ ከኤፉዱ ጋራ አንድ ወጥ የሆነና ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ በቀጭኑ ከተፈተለ ሐር የተሠራ ነበረ።
6የከበሩ መረግዶችን በወርቅ ፈርጦች በመክፈፍ፣ እንደ ማኅተም የእስራኤልን ልጆች ስሞች ቀረጹባቸው። 7ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው በኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ላይ ለእስራኤል ልጆች እንደ መታሰቢያ ድንጋዮች አያያዟቸው።
የደረት ኪስ
39፥8-21 ተጓ ምብ – ዘፀ 28፥15-28
8የደረት ኪሱንም ጥበበኛ ባለሙያ እንደሚሠራው ሥራ በተመሳሳይ መንገድ ሠሩት፤ እንደ ኤፉዱም ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ በቀጭኑም ከተፈተለ በፍታ ሠሩት። 9ርዝመቱ አንድ ስንዝር ወርዱም አንድ ስንዝር#39፥9 ወደ 23 ሳንቲ ሜትር ያህል ነው። ሲሆን፣ ጥንድ ድርብ ሆኖ ባለአራት ማእዘን ነበረ። 10ከዚያም የከበሩ ድንጋዮችን በአራት ረድፍ በላዩ ላይ አደረጉበት፤ በመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፣ ቶጳዝዮንና የሚያብረቀርቅ ዕንቍ ነበር፤ 11በሁለተኛውም ረድፍ በሉር፣ ሰንፔርና#39፥11 ወይም ላፒስ ላዙሊ አልማዝ፣ 12በሦስተኛውም ረድፍ ያክንት፣ ኬልቄዶንና አሜቴስጢኖስ፣ 13በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያሰጲድ#39፥13 ከእነዚህ የከበሩ ማዕድኖች መካከል አንዳንዶቹ ማንነታቸው አይታወቅም። ነበረ፤ በወርቅ ፈርጥ ላይ ተደርገው ነበር። 14ለእያንዳንዱ የእስራኤል ልጆች ስም አንዳንድ ሆኖ፣ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ማኅተም ከዐሥራ ሁለቱ ነገዶች የአንዱ ስም የተቀረጸበት ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ነበሩ።
15ለደረት ኪሱም ልክ እንደ ገመድ ከንጹሕ ወርቅ የተጐነጐኑ ድሪዎችን አበጁለት። 16ሁለት የወርቅ ፈርጦችንና ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ቀለበቶቹን ከደረት ኪሱ ሁለት ጐኖች ጋራ አያያዟቸው። 17ሁለቱን የወርቅ ድሪዎች በደረት ኪሱ ጐንና ጐን ካሉት ቀለበቶች ጋራ አያያዟቸው፤ 18የድሪዎቹን ሌሎች ጫፎች ከፊት ካለው ከኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ጋራ በማገናኘት ከሁለቱ የወርቅ ፈርጦች ጋራ አያያዟቸው። 19ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ከኤፉዱ ቀጥሎ ካሉት ከሌሎቹ ሁለት የደረት ኪስ ጐኖች ጋራ ከውስጠኛው ጠርዝ ላይ አያያዟቸው። 20ከዚያም ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ልክ ከኤፉዱ መታጠቂያ በላይ፣ ከመጋጠሚያው አጠገብ፣ ከኤፉዱ ፊት ለፊት ካሉት ከትከሻ ንጣዮች ጋራ አያያዟቸው። 21እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ተነጥሎ ለብቻው እንዳይንጠለጠል የደረት ኪሱን ቀለበቶች ከመታጠቂያው ጋራ በማገናኘት፣ ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋራ በሰማያዊ ፈትል አሰሯቸው።
ሌሎች የካህናት አልባሳት
39፥22-31 ተጓ ምብ – ዘፀ 28፥31-43
22የኤፉዱን ቀሚስ በሸማኔ ሥራ ሙሉ በሙሉ ከሰማያዊ ጨርቅ ሠሩት፤ 23ይህም እንደ ክሳዱ ቅድ ከቀሚሱ መካከል ላይ ዐንገትጌ#39፥23 በዕብራይስጡ የዚህ ቃል ትርጕም በትክክል አይታወቅም። ነበረው፤ እንዳይተረተርም በዐንገትጌው ዙሪያ ላይ ቅምቅማት ነበረው። 24በቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ ላይ ሮማኖቹን አደረጉ። 25ከንጹሕ ወርቅም ሻኵራዎችን ሠሩ፤ እነዚህንም በሮማኖቹ መካከል በጠርዙ ዙሪያ አደረጉ። 26እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለአገልግሎት ይለበሱ ዘንድ ሻኵራዎቹና ሮማኖቹ በቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ ላይ ተሰባጥረው ይገኙ ነበር።
27ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ የሸማኔ ሥራ የሆነውን ከቀጭን በፍታ ሸሚዞችን ሠሩ፤ 28እንዲሁም ከቀጭን በፍታ ጥምጥምን፣ የሐር ቆቦቹንና በቀጭኑ ከተፈተለም በፍታ ሱሪዎችን ሠሩ። 29መታጠቂያው እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታና ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ የጥልፍ ጠላፊ ሥራ ሆኖ የተሠራ ነበረ።
30ከንጹሕ ወርቅ የተቀደሰውን አክሊል ሰሌዳ ሠርተው፣ በማኅተም ላይ እንደ ተቀረጸ ጽሑፍ፤
ቅዱስ ለእግዚአብሔር
የሚል ቀረጹበት። 31ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ከመጠምጠሚያው ጋራ ለማያያዝ ሰማያዊ ፈትል አሰሩበት።
ሙሴ የማደሪያውን ድንኳን መቈጣጠሩ
39፥32-41 ተጓ ምብ – ዘፀ 35፥10-19
32በዚህ መሠረት የማደሪያው ድንኳን፣ የመገናኛው ድንኳን ሥራ በሙሉ ተጠናቀቀ። እስራኤላውያን ልክ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉን ነገር ሠሩ። 33ከዚያም የማደሪያውን ድንኳን ወደ ሙሴ አመጡት፦
እነዚህም ድንኳንና ዕቃዎቹ ሁሉ፣ ማያያዣዎችን፣ ክፈፎችን፣ አግዳሚዎችን፣ ቋሚዎችንና መሠረቶችን፤
34ቀይ ከተነከረ የአውራ በግ ቈዳ የተሠራ መደረቢያ፣ የለፋ የአቆስጣ ቈዳ#39፥34 ይህ የባሕር አውሬ ነው። መደረቢያና መከለያ መጋረጃ፤
35የምስክሩ ታቦት፣ ከመሎጊያዎቹና ከስርየት መክደኛው ጋራ፤
36ጠረጴዛውን ከነመሎጊያዎቹ ዕቃዎቹን ሁሉና ከገጸ ኅብስቱ ጋራ፤
37ከንጹሕ ወርቅ የሆነው መቅረዝ ከተደረደሩት መብራቶችና ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋራ፣ የመብራቱም ዘይት፤
38የወርቅ መሠዊያው፣ ቅብዐ ዘይቱ፣ መልካም መዐዛ ያለው ዕጣን እንዲሁም የድንኳኑ መግቢያ መጋረጃ፤
39የንሓስ መሠዊያው ከንሓስ መጫሪያው፣ መሎጊያዎቹና ዕቃዎቹ ሁሉ ጋራ፤
የመታጠቢያው ሳሕን ከነማስቀመጫው፤
40የአደባባዩ መጋረጃዎች ከምሰሶዎቹና ከመቆሚያዎቹ ጋራ፣ የአደባባዩ መግቢያ መጋረጃ፤
ገመዶቹና የአደባባዩ ድንኳን ካስማዎች፤
የማደሪያው የመገናኛው ድንኳን ዕቃዎች ሁሉ፤
41በመቅደሱ ሲያገለግሉ የሚለበሱት የተፈተሉት ቀሚሶች፣ ለካህኑ ለአሮን የተቀደሱት ቀሚሶችና ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚያደርጓቸው ቀሚሶች ናቸው።
42እስራኤላውያን ልክ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሥራውን ሁሉ አከናወኑ። 43ሙሴ ሥራውን አየ፤ ልክ እግዚአብሔር እንዳዘዘው መሥራታቸውንም ተመለከተ፤ ስለዚህ ባረካቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.