ሕዝቅኤል 41
41
1ከዚያም ወደ መቅደሱ አገባኝ፤ ዐምዶቹንም ለካ፤ የዐምዶቹም ወርድ#41፥1 አንድ የዕብራይስጥ የጥንት ቅጅና ሰብዓ ሊቃናት እንዲሁ ሲሆኑ አብዛኛዎቹ የዕብራይስጥ የጥንት ቅጆች ግን …የድንኳኑ ወርድ ይላሉ። በአንዱ በኩል ስድስት ክንድ#41፥1 3.2 ሜትር ይሆናል በቍጥር 3፣ 5 እና 8፣ በሌላውም በኩል ስድስት ክንድ ነበር። 2የመግቢያውም በር ወርድ ዐሥር ክንድ#41፥2 5.3 ሜትር ሲሆን፣ በግራና በቀኝ በኩል ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦች ወርድ ዐምስት ክንድ#41፥2 2.7 ሜትር በቍጥር 9፣ 11 እና 12 ነበር። ደግሞም የውስጡን መቅደስ ለካ፤ ርዝመቱ አርባ ክንድ፣ ወርዱም ሃያ ክንድ#41፥2 21 ሜትር ርዝመትና 11 ሜትር ወርድ ነበር።
3ከዚያም ወደ ውስጥ ገባ፤ የመግቢያውን ዐምዶች ለካ፤ የእያንዳንዱም ወርድ ሁለት ክንድ#41፥3 1.1 ሜትር በተጨማሪ ቍጥር 22 ነበር። የመግቢያውም ወርድ ስድስት ክንድ ሲሆን፣ ግራና ቀኝ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦች ወርድ ደግሞ ሰባት ክንድ#41፥3 3.7 ሜትር ነበር። 4እርሱም የውስጠኛውን መቅደስ ርዝመት ለካ፤ ሃያ ክንድ ነበር፤ ወርዱም የውጪውን ግድግዳ ጨምሮ ሃያ ክንድ ነበር፤ እርሱም፣ “ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው” አለኝ።
5ከዚያም የቤተ መቅደሱን ግንብ ለካ፤ ውፍረቱ ስድስት ክንድ ነው፤ በቤተ መቅደሱ ግንብ ዙሪያ ግራና ቀኝ ያለው የእያንዳንዱ ክፍል ወርድ አራት ክንድ#41፥5 2.1 ሜትር ነበር። 6ግራና ቀኝ ያሉት ክፍሎች፣ ባለሦስት ደርብ ናቸው፤ በእያንዳንዱም ደርብ ላይ ሠላሳ ክፍሎች ነበሩ፤ በግንቡም ዙሪያ ግራና ቀኝ ያሉትን እነዚህን ክፍሎች ደግፈው የሚይዙ ተሸካሚዎች ነበሩ፤ ሆኖም ተሸካሚዎቹ ወደ ቤተ መቅደሱ ግንብ ዘልቀው አልገቡም ነበር። 7በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ያሉት ክፍሎች ስፋት በየደርቡ እየጨመረ የሚሄድ ነው። በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ያለው ሕንጻ አሠራሩ ከታች ወደ ላይ እየሰፋ የሚሄድ በመሆኑ፣ ወደ ላይ በተሄደ ቍጥር የክፍሎቹ ስፋት እየጨመረ የሚሄድ ነው። በመካከለኛው ደርብ በኩል አድርጎ ከታች ወደ ላይ የተዘረጋም ደረጃ አለ።
8ቤተ መቅደሱ ዙሪያውን ከፍ ብሎ የተሠራ መሠረት ያለው መሆኑን አየሁ፤ ይህ ግራና ቀኝ ላሉት ክፍሎች መሠረት ሲሆን፣ ርዝመቱ ስድስት ክንድ ነው፤ ይህም የዘንጉ ቁመት ነበር። 9በውጭ በኩል ያለው የግራና የቀኙ ክፍሎች ግንብ ውፍረት ዐምስት ክንድ ነበር፤ ክፍቱ ቦታ በቤተ መቅደሱና 10በካህናቱ ክፍሎች መካከል ያለ ሲሆን፣ ስፋቱ በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ሃያ ክንድ ነበር። 11ከክፍቱ ቦታ ግራና ቀኝ ወዳሉ ክፍሎች የሚያስገቡ በሮች ነበሩ። አንዱ በሰሜን በኩል ሲሆን፣ ሌላው በር ደግሞ በደቡብ በኩል ነው። ክፍቱን ቦታ ዙሪያውን የሚያገናኘው መሠረት ስፋቱ ዐምስት ክንድ ነው።
12በምዕራብ በኩል ከቤተ መቅደሱ ግቢ ትይዩ የሆነው ሕንጻ ወርድ ሰባ ክንድ#41፥12 37 ሜትር ነበር። የሕንጻው ግንብ ውፍረት ዙሪያውን ዐምስት ክንድ ሲሆን፣ ርዝመቱ ዘጠና ክንድ#41፥12 48 ሜትር ነበር።
13ከዚያም ቤተ መቅደሱን ለካ፤ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ#41፥13 53 ሜትር በተጨማሪም ቍጥር 14 እና 15 ሲሆን፣ የቤተ መቅደሱ ግቢና ሕንጻ ከነግንቡ ደግሞ አንድ መቶ ክንድ ሆነ። 14በምሥራቅ በኩል የቤተ መቅደሱ ግቢ ስፋት፣ ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን ስፍራ ጨምሮ አንድ መቶ ክንድ ነበር።
15ከዚያም ከቤተ መቅደሱ በስተጀርባ ከግቢው ትይዩ ያለውን ሕንጻ ለካ፤ ይህም በግራና በቀኝ ያሉትን መተላለፊያዎች የሚጨምር ሲሆን፣ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ነበር።
የውጩ መቅደስና የውስጡ መቅደስ ከአደባባዩ ትይዩ ያለው መተላለፊያ በረንዳ፣ 16እንዲሁም መድረኮቹና ጠበብ ያሉት መስኮቶች፣ በሦስቱም ዙሪያ ያሉት መተላለፊያዎች፣ ከመድረኩ በላይና ራሱ መድረኩም ጭምር ሁሉም በዕንጨት ተለብዶ ነበር። ወለሉ፣ እስከ መስኮቶቹ ያለው ግንብና መስኮቶቹ ተለብደዋል። 17ከውስጡ መቅደስ መግቢያ በላይ ያለው ውስጡና ውጩ እንዲሁም በውስጡ መቅደስና በውጩ መቅደስ መካከል ያለው ሁሉ ዙሪያውን 18ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ ተቀርጸውበት ነበር፤ የዘንባባ ዛፎቹ የተቀረጹት በኪሩብና በኪሩብ መካከል ነበር። እያንዳንዱም ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው፤ 19የሰው ፊት ያለው ኪሩብ በአንድ በኩል ወዳለው ዘንባባ የዞረ ሲሆን፣ የአንበሳ ፊት ያለውም በሌላ በኩል ወዳለው ዘንባባ ዞሮ ነበር። ሁሉም በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ላይ ተቀርጸው ነበር። 20ከወለሉ አንሥቶ ከመግቢያው በላይ እስካለው ስፍራ ድረስ፣ የውስጡ መቅደስ የውጭ ግድግዳ ላይ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ ተቀርጿል።
21የውስጡ መቅደስ በር መቃን ባለአራት ማእዘን ነበር፤ ከቅድስተ ቅዱሳኑም ፊት ለፊት ያለው በር እንዲሁ ባለአራት ማእዘን ነበር። 22ሦስት ክንድ ቁመት፣ ሁለት ክንድ#41፥22 ሰብዓ ሊቃናቱ እንዲሁ ሲሆን፣ ዕብራይስጡ ግን ርዝመቱ ሁለት ወርድ ይላል ወርድ፣ ሁለት ክንድ ርዝመት ያለው የዕንጨት መሠዊያ ነበር፤ ማእዘኖቹ፣ መሠረቱና#41፥22 ሰብዓ ሊቃናቱ እንዲሁ ሲሆን፣ ዕብራይስጡ ግን ርዝመቱ ይላል ጐኖቹ ሁሉ ከዕንጨት የተሠሩ ነበሩ። ሰውየውም፣ “ይህች በእግዚአብሔር ፊት ያለች ገበታ ናት” አለኝ። 23የውስጡ መቅደስና ቅድስተ ቅዱሳኑ እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት በር አላቸው፤ 24እያንዳንዱ በር መካከሉ ላይ በመታጠፊያ የተያያዙ መዝጊያዎች አሉት። 25በግንቦቹ ላይ እንዳለው ሁሉ በውስጡ መቅደስ በሮችም ላይ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፎች ተቀርጸዋል፤ በመተላለፊያ በረንዳውም ፊት ለፊት የዕንጨት መዝጊያ ተንጠልጥሏል። 26በመተላለፊያ በረንዳውም ግራና ቀኝ ግንብ ላይ የዘንባባ ዛፍ ቅርጽ ያለባቸው ጠባብ መስኮቶች ነበሩ። ግራና ቀኝ ያሉት ክፍሎችም በደረጃው በኩል የሚሸፍን ጣራ ነበራቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.