ሕዝቅኤል 42
42
ለካህናት የተመደቡ ክፍሎች
1ከዚያም ያ ሰው በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ውጩ አደባባይ በማምጣት፣ በቤተ መቅደሱ አደባባይ ትይዩና በሰሜን በኩል ባለው ግንብ ትይዩ ወደ አሉት ክፍሎች አመጣኝ። 2በሩ በሰሜን ትይዩ የሆነው ሕንጻ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ወርዱም ዐምሳ ክንድ ነበር።#42፥2 53 ሜትር ርዝመትና 27 ሜትር ስፋት 3ከውስጠኛው አደባባይ ሃያ ክንድ#42፥3 11 ሜትር ርቀት ላይና በአንጻሩም ከውጩ አደባባይ የንጣፍ ድንጋይ ፊት ለፊት ርቀት ላይ በሦስት ደርቦች ትይዩ የሆኑ ሰገነቶች ነበሩ። 4ከክፍሎቹ ፊት ለፊት ወርዱ ዐሥር ክንድ፣ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ#42፥4 5.3 ሜትር ስፋትና 53 ሜትር ርዝመት የሆነ መተላለፊያ በውስጥ በኩል ነበር። የክፍሎቹም በሮች በሰሜን በኩል ነበሩ። 5የላይኞቹ ክፍሎች ጠበብ ያሉ ናቸው፤ ምክንያቱም ሰገነቶቹ ታችና መካከል ላይ ካሉት ከሕንጻው ክፍሎች ይልቅ ሰፋ ያሉ ቦታዎች ይዘውባቸዋልና። 6አደባባዮቹ ዐምዶች ሲኖሯቸው፣ በሦስተኛው ደርብ ላይ ያሉት ክፍሎች ግን ዐምድ የላቸውም። ስለዚህ የወለላቸው ስፋት በታችኛውና በመካከለኛው ደርብ ካሉት ክፍሎች ይልቅ ጠበብ ያለ ነው። 7ከክፍሎቹና፣ ከውጩ አደባባይ ትይዩ የሆነ የውጪ ግንብ አለ፤ ይህም በክፍሎቹ ፊት ለፊት ሆኖ ዐምሳ ክንድ ይረዝማል። 8ከውጩ አደባባይ ቀጥሎ ያሉት መደዳ ክፍሎች ርዝመት ዐምሳ ክንድ ሲሆን፣ ከቤተ መቅደሱ አጠገብ ያሉት መደዳ ክፍሎች ርዝመት ደግሞ አንድ መቶ ክንድ ነበር። 9ከውጩ አደባባይ ወደ ውስጥ ሲገባ፣ በስተምሥራቅ የታችኞቹ ክፍሎች መግቢያ ይገኛል።
10በደቡብ በኩል#42፥10 ሰብዓ ሊቃናቱም እንዲሁ ሲሆን ዕብራይስጡ ግን በስተምሥራቅ ይላል የውጩን አደባባይ ግንብ ተከትሎ፣ ከቤተ መቅደሱ አደባባይ ጋራ የተያያዙና ከውጩ ግንብ ጋራ ትይዩ የሆኑ ክፍሎች አሉ፤ 11ከፊት ለፊታቸውም መተላለፊያ መንገድ አለ። እነዚህ በሰሜን በኩል ካሉት ክፍሎች ጋራ ተመሳሳይ ሲሆኑ፣ ርዝመትና ወርዳቸው፣ መውጫና መጠናቸው አንድ ዐይነት ነበር፤ በሰሜን በኩል እንዳሉት በሮች፣ 12በደቡብ በኩል ያሉት ክፍሎች በሮች መጠናቸው ተመሳሳይ ነበር። ከመመላለሻው መነሻ ላይ መግቢያ በር አለ፤ መመለሻውም ፊት ለፊት ካለው ወደ ምሥራቅ ከሚያመራው ግንብ ጋራ ተጓዳኝ ነው።
13ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ከቤተ መቅደሱ አደባባይ ፊት ለፊት ያሉት የሰሜኑና የደቡቡ ክፍሎች የካህናቱ ሲሆኑ፣ እነዚህም በእግዚአብሔር ፊት የሚቀርቡት ካህናት እጅግ የተቀደሱትን ቍርባኖች የሚበሉባቸው ናቸው። በዚያም እጅግ የተቀደሱትን ቍርባኖች ማለት የእህሉን ቍርባን፣ የኀጢአቱን ቍርባን፣ የበደሉን ቍርባን ያስቀምጣሉ፤ ቦታው ቅዱስ ነውና። 14ካህናቱ አንድ ጊዜ ወደ ተቀደሰው ቦታ ከገቡ በኋላ፣ ያገለገሉበትን ልብስ ሳያወልቁ ወደ ውጩ አደባባይ መውጣት አይችሉም፤ የተቀደሰ ነውና፤ ወደ ሕዝቡ ቦታ ከመምጣታቸው በፊት ሌላውን ልብሳቸውን መልበስ አለባቸው።”
15በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለውን ስፍራ ለክቶ ከጨረሰ በኋላ፣ በምሥራቅ በር በኩል ወደ ውጩ አወጣኝ፤ በዙሪያው ያለውንም ስፍራ ሁሉ ለካ፤ 16በምሥራቅ ያለውንም በመለኪያው ዘንግ ለካ፤ ዐምስት መቶ ክንድ#42፥16 ከሰብዐ ሊቃናት 17ን ይመ፤ ዕብራይስጡ ግን ዘንጎች ይለዋል፤ እንዲሁም 18 እና 19 ሆነ። 17ሰሜኑንም ለካ፤ በመለኪያው ዘንግ ዐምስት መቶ ክንድ#42፥17 ሰብዓ ሊቃናቱም እንዲሁ ሲሆን፣ ዕብራይስጡ ግን ዘንጎች ይላል ሆነ። 18ደቡቡንም ለካ፤ በመለኪያው ዘንግ ዐምስት መቶ ክንድ ሆነ። 19ከዚያም ወደ ምዕራብ ጐን ዞሮ ለካ፤ በመለኪያው ዘንግ ዐምስት መቶ ክንድ ሆነ። 20ስለዚህ በአራቱም ማእዘን ለካው፤ የተቀደሰውን ስፍራ ከሌላው የሚለይ በዙሪያው ግንብ ነበረ፤ የግንቡም ርዝመት ዐምስት መቶ ክንድ ሲሆን፣ ወርዱ ዐምስት መቶ ክንድ ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.