ኢሳይያስ 12
12
የውዳሴ መዝሙር
1በዚያ ቀን እንዲህ ትላለህ፤
“እግዚአብሔር ሆይ፤
ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤
አሁን ግን ከቍጣህ ተመለስህ፤
ደግሞም አጽናንተኸኛልና አወድስሃለሁ።
2እነሆ፣ አምላክ ድነቴ ነው፤
እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤
ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ#12፥2 ወይም ዝማሬዬ ነው፤
ድነቴም ሆኗል።”
3ከድነቴ ምንጮች
ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ።
4በዚያ ቀን እንዲህ ትላላችሁ፤
“እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤
ያደረገውንም በአሕዛብ መካከል አስታውቁ፤
ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱንም ዐውጁ።
5ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ታላቅ ሥራ ሠርቷልና፤
ይህም ለዓለም ሁሉ ይታወቅ።
6የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤
በደስታም ዘምሩ፤
በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።”
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.