የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢሳይያስ 34

34
ፍርድ በአሕዛብ ላይ
1እናንተ አሕዛብ ሆይ፤ ኑ አድምጡም፤
እናንተ ሰዎች ሆይ፤ አስተውሉ።
ምድርና በውስጧ ያለ ሁሉ፣
ዓለምና ከርሷ የሚበቅል ሁሉ ይስማ!
2 እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ ተቈጥቷል፤
ቍጣውም በሰራዊታቸው ሁሉ ላይ ነው፤
ፈጽሞ ያጠፋቸዋል#34፥2 በዚህና በቍጥር 5 ላይ የዕብራይስጡ ቃል አንድን ሰው ወይም ነገር ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ለእግዚአብሔር መስጠትን የሚያመለክት ነው።
ለዕርድም አሳልፎ ይሰጣቸዋል።
3ከእነርሱም የተገደሉት ወደ ውጭ ይጣላሉ፤
ሬሳቸው ይከረፋል፤
ተራሮችም ደም በደም ይሆናሉ።
4የሰማይ ከዋክብት ሁሉ ይሟሽሻሉ፤
ሰማይ እንደ ብራና ይጠቀለላል፤
የከዋክብት ሰራዊት ሁሉ፣
ጠውልጎ እንደ ረገፈ የወይን ቅጠል፣
ደርቆም እንደ ወደቀ የበለስ ቅጠል ይሆናሉ።
5ሰይፌ በሰማያት እስኪበቃት ጠጥታለች፤
እነሆ፤ ወደ ኤዶም፣
ፈጽሞ ወዳጠፋሁት ሕዝብ ለፍርድ ወርዳለች።
6እግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተነክራለች፤
ሥብ ጠግባለች፤
በበግ ጠቦትና በፍየል ደም፣
በአውራም በግ ኵላሊት ሥብ ተሸፍናለች።
እግዚአብሔር በባሶራ ከተማ መሥዋዕት፣
በኤዶምም ታላቅ ዕርድ አዘጋጅቷልና።
7ጐሽ ዐብሯቸው፣
ኰርማም ከወይፈን ጋራ ይወድቃል፤
ምድራቸው በደም ትርሳለች፤
ዐፈራቸውም ሥብ በሥብ ይሆናል።
8 እግዚአብሔር የበቀል ቀን፣
ስለ ጽዮንም የሚሟገትበት ዓመት አለውና።
9የኤዶም ምንጮች ሬንጅ፣
ዐፈሯ የሚቃጠል ድኝ፣
ምድሯም የሚንበለበል ዝፍት ይሆናል!
10እሳቷ ሌሊትና ቀን አይጠፋም፤
ጢሷም ለዘላለም ይትጐለጐላል፤
ከትውልድ እስከ ትውልድ ባድማ ትሆናለች፤
ማንም በዚያ ዳግም አያልፍም።
11ጭልፊትና#34፥11 የእነዚህ አዕዋፍ ትክክለኛ ማንነታቸው በትክክል አይታወቅም። ጃርት ይወርሷታል፤
ጕጕትና ቍራም ጐጆ ይሠሩባታል።
እርሱ በኤዶም ላይ፣
የመፈራረሷን ገመድ፣
የመጥፊያዋንም ቱንቢ ይዘረጋል።
12መኳንንቷም መንግሥት ተብለው ለመጠራት
የሚያስችላቸው ነገር አይኖራቸውም፤
አለቆቿም በሙሉ ጥርግ ብለው ይጠፋሉ።
13በቅጥር የተመሸጉ ከተሞቿን እሾኽ፣
ምሽጎቹንም ሳማና አሜከላ ይወርሷቸዋል፤
የቀበሮዎች ጕድጓድ፣
የጕጕቶችም መኖሪያ ትሆናለች።
14የምድረ በዳ አራዊት ከጅቦች ጋራ ዐብረው ይሆናሉ፤
በበረሓ ፍየል የሚመሰሉ አጋንንትም እርስ በእርስ ይጠራራሉ፤
የሌሊት ፍጥረታት ማረፊያቸውን በዚያ ያደርጋሉ፤
ለራሳቸውም የማረፊያ ቦታ ያገኛሉ።
15ጕጕት በዚያ ጐጆ ሠርታ ዕንቍላል ትጥላለች፤
ትቀፈቅፋለች፤ ጫጩቶቿን በክንፎቿ
ትታቀፋቸዋለች፤
ጭላቶችም ጥንድ ጥንድ ሆነው፣
ለርቢ በዚያ ይሰበሰባሉ።
16እግዚአብሔር መጽሐፍ እንዲህ የሚለውን ተመልከቱ፤ አንብቡም፤
ከእነዚህ አንዱ አይጐድልም፤
እያንዳንዷም አጣማጇን አታጣም፤
ይህ ትእዛዝ ከአፉ ወጥቷል፤
መንፈሱ በአንድ ላይ ይሰበስባቸዋልና።
17ድርሻ ድርሻቸውን ይመድብላቸዋል፤
እጁም ለክታ ታካፍላቸዋለች።
ለዘላለም የእነርሱ ትሆናለች፤
ከትውልድ እስከ ትውልድም ይኖሩባታል።

Currently Selected:

ኢሳይያስ 34: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ