ኢያሱ 12
12
የተሸነፉ ነገሥታት ስም ዝርዝር
1እንግዲህ እስራኤላውያን ድል ያደረጓቸውና ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምሥራቅ የሚገኘውን የዓረባን ክፍል በሙሉ ይዞ፣ ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንዔም ተራራ የሚዘልቀውን ግዛታቸውን የወሰዱባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤
2መቀመጫውን በሐሴቦን አድርጎ የገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፣
ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ላይ ካለችው ከአሮዔር ማለት ከሸለቆው መካከል አንሥቶ፣ የአሞናውያን ወሰን እስከ ሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ ገዝቷል፤ ይህም የገለዓድን እኩሌታ ይጨምራል።
3እንዲሁም ከኪኔሬት ባሕር#12፥3 “ገሊላ” ናት። እስከ ጨው#12፥3 የጨው ባሕር፣ የሙት ባሕርም ይባላል። ባሕር ያለውን ምሥራቃዊውን ዓረባ፣ እስከ ቤትየሺሞትና ከዚያም በስተ ደቡብ እስከ ፈስጋ ተራራ ግርጌ ድረስ ገዝቷል።
4መቀመጫውን በአስታሮትና በኤድራይ አድርጎ የገዛውና ከመጨረሻዎቹ ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነው የባሳን ንጉሥ ዐግ፣
5የአርሞንዔምን ተራራ፣ ሰልካንን፣ ባሳንን ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ድንበሮች እንዲሁም ከገለዓድ እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ወሰን ድረስ ገዝቷል።
6የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴና እስራኤላውያን እነዚህን ድል አደረጉ፤ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴም ምድራቸውን ለሮቤል፣ ለጋድና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርጎ ሰጣቸው።
7እንግዲህ ኢያሱና እስራኤላውያን ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ ድል ያደረጓቸው የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ ግዛታቸውም በሊባኖስ ሸለቆ ውስጥ ካለው ከበኣልጋድ ተነሥቶ በምዕራብ ሴይር እስካለው እስከ ሐላቅ ተራራ ይደርሳል፤ ኢያሱም የእነዚህን ነገሥታት ምድር እንደ ነገዳቸው አከፋፈል ለእስራኤላውያን በማከፋፈል ርስት አድርጎ ሰጣቸው። 8ይህም ተራራማው አገር፤ በስተምዕራብ ያለው የኰረብታ ግርጌ፣ ዓረባ፣ የተራራው ሸንተረሮች፣ ምድረ በዳውና ኔጌብ ማለት የኬጢያውያን፣ የአሞራውያን፣ የከነዓናውያን፣ የፌርዛውያን፣ የኤዊያውያንና የኢያቡሳውያን ምድር ነው።
ነገሥታቱም እነዚህ ናቸው፤
9የኢያሪኮ ንጉሥ፣ አንድ
ቤቴል አጠገብ ያለችው የጋይ ንጉሥ፣ አንድ
10የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ አንድ
የኬብሮን ንጉሥ፣ አንድ
11የያርሙት ንጉሥ፣ አንድ
የለኪሶ ንጉሥ፣ አንድ
12የዔግሎን ንጉሥ፣ አንድ
የጌዝር ንጉሥ፣ አንድ
13የዳቤር ንጉሥ፣ አንድ
የጌድር ንጉሥ፣ አንድ
14የሖርማ ንጉሥ፣ አንድ
የዓራድ ንጉሥ፣ አንድ
15የልብና ንጉሥ፣ አንድ
የዓዶላም ንጉሥ፣ አንድ
16የመቄዳ ንጉሥ፤ አንድ
የቤቴል ንጉሥ፣ አንድ
17የታጱዋ ንጉሥ፣ አንድ
የኦፌር ንጉሥ፣ አንድ
18የአፌቅ ንጉሥ፣ አንድ
የሳሮን ንጉሥ፣ አንድ
19የማዶን ንጉሥ፣ አንድ
የአሦር ንጉሥ፣ አንድ
20የሺምሮን ሚሮን ንጉሥ፣ አንድ
የአዚፍ ንጉሥ፣ አንድ
21የታዕናክ ንጉሥ፣ አንድ
የመጊዶ ንጉሥ፣ አንድ
22የቃዴስ ንጉሥ፣ አንድ
በቀርሜሎስ የሚገኘው የዮቅንዓም ንጉሥ፣ አንድ
23በዶር ኰረብታ#12፥23 ወይም፣ “ናፎት ዳር” ማለት ነው። የሚገኘው የዶር ንጉሥ፣ አንድ
በጌልገላ የሚገኘው የጎይም ንጉሥ፣ አንድ
24የቴርሳ ንጉሥ፣ አንድ
እነዚህ በድምሩ ሠላሳ አንድ ነገሥታት ናቸው።
Currently Selected:
ኢያሱ 12: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.