ዘሌዋውያን 27

27
ስለ ስጦታ የወጣ ሕግ
1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘ማንኛውም ሰው ተመጣጣኙን ዋጋ በመክፈል ለእግዚአብሔር ሰውን ለመስጠት የተለየ ስእለት ቢሳል፣ 3ዕድሜው ከሃያ እስከ ስድሳ ዓመት ለሆነ ወንድ፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል#27፥3 0.6 ኪሎ ግራም ገደማ ይሆናል፤ እንዲሁም 16 ይመ ሚዛን መሠረት፣ ግምቱ ዐምሳ ጥሬ ሰቅል#27፥3 11.5 ግራም ገደማ ይሆናል፤ እንዲሁም 25 ይመ ብር ይሁን። 4ለሴት ከሆነ ግምቱ ሠላሳ ሰቅል#27፥4 0.3 ኪሎ ግራም ገደማ ይሆናል ይሁን። 5ዕድሜው ከዐምስት እስከ ሃያ ዓመት ለሆነ ሰው፣ ወንድ ከሆነ ግምቱ ሃያ ሰቅል፣#27፥5 0.2 ኪሎ ግራም ገደማ ይሆናል ሴት ከሆነች ግምቷ ዐሥር ሰቅል#27፥5 110 ግራም ገደማ ይሆናል፤ እንዲሁም 7 ይመ ይሁን። 6ዕድሜው ከአንድ ወር እስከ ዐምስት ዓመት ለሆነ ሰው፣ ወንድ ከሆነ ግምቱ ዐምስት ሰቅል#27፥6 55 ግራም ገደማ ይሆናል ጥሬ ብር፣ ለሴት ከሆነ ሦስት ሰቅል#27፥6 35 ግራም ገደማ ይሆናል ጥሬ ብር ይሁን። 7ስድሳ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ለሆነ ሰው፣ ወንድ ከሆነ ግምቱ ዐሥራ ዐምስት ሰቅል፣ ሴት ከሆነች ዐሥር ሰቅል ይሁን። 8ስእለት የተሳለው ድኻ ከሆነና ግምቱን መክፈል ካልቻለ ግን፣ ለስጦታ ያሰበውን ሰው ወደ ካህኑ ያምጣ፤ ካህኑም የተሳለው ሰው ባለው ዐቅም መሠረት መክፈል የሚገባውን ይተምንለታል።
9“ ‘ሰውየው የተሳለው ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሆኖ መቅረብ የሚችል እንስሳ ከሆነ፣ እንዲህ ያለው ለእግዚአብሔር የተሰጠ እንስሳ የተቀደሰ ይሆናል። 10ሰውየው መልካም የሆነውን እንስሳ መልካም ባልሆነው፣ መልካም ያልሆነውንም መልካም በሆነው አይለውጥ ወይም አይተካ፤ አንዱን እንስሳ በሌላው ከተካም ሁለቱ የተቀደሱ ይሆናሉ። 11እንስሳው በሥርዐቱ መሠረት የረከሰ፣ ለእግዚአብሔርም መሥዋዕት ሆኖ መቅረብ የማይገባው ከሆነ፣ ሰውየው እንስሳውን ወደ ካህኑ ያቅርብ፤ 12መልካም ቢሆን ወይም ባይሆን፣ ካህኑ ዋጋውን ይወስን፤ የካህኑም ውሳኔ የጸና ይሆናል። 13ባለቤቱ እንስሳውን መዋጀት ከፈለገ ግን፣ በተተመነው ዋጋ ላይ አንድ ዐምስተኛ መጨመር አለበት።
14“ ‘አንድ ሰው ቤቱን ለእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ ቢቀድስ፣ መልካም ቢሆን ወይም ባይሆን ካህኑ ዋጋውን ይተምን፤ ካህኑም የተመነው ዋጋ የጸና ይሆናል። 15ቤቱን የቀደሰው ሰው መልሶ ሊዋጀው ከፈለገ ግን፣ የዋጋውን አንድ ዐምስተኛ በዋጋው ላይ መጨመር አለበት፤ ቤቱም ዳግመኛ የራሱ ይሆናል።
16“ ‘አንድ ሰው ከወረሰው ርስት ላይ ለእግዚአብሔር የዕርሻ መሬት ቢቀድስ፣ ዋጋው የሚተመነው ለመሬቱ በሚያስፈልገው ዘር መጠን ይሆናል፤ ይኸውም ለአንድ ሆሜር#27፥16 220 ሊትር ገደማ ይሆናል መስፈሪያ የገብስ ዘር ዐምሳ ሰቅል ጥሬ ብር ነው። 17ሰውየው ዕርሻውን የቀደሰው በኢዮቤልዩ ዓመት ከሆነ፣ የተወሰነው ዋጋ አይለወጥም። 18ዕርሻውን የሚቀድሰው ከኢዮቤልዩ በኋላ ከሆነ ግን፣ ካህኑ ዋጋውን የሚተምነው እስከሚመጣው የኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ባሉት ዓመታት ቍጥር ልክ ነው፤ የተተመነውም ዋጋ ይቀነሳል። 19ዕርሻውን የቀደሰው ሰው መልሶ መዋጀት ከፈለገ፣ በዋጋው ላይ አንድ ዐምስተኛ መጨመር አለበት፤ ከዚያ በኋላ ዕርሻው እንደ ገና የራሱ ይሆናል። 20ዕርሻውን ባይዋጅ ወይም ለሌላ ሰው አሳልፎ ቢሸጥ፣ ከዚያ በኋላ ሊዋጀው አይችልም። 21ዕርሻው በኢዮቤልዩ በሚለቀቅበት ጊዜ ለእግዚአብሔር እንደ ተሰጠ ዕርሻ ተቈጥሮ ቅዱስና የካህናቱ#27፥21 ወይም የካህኑ ንብረት ይሆናል።
22“ ‘አንድ ሰው የወረሰው ርስት ያልሆነውን፣ በገንዘቡ የገዛውን የዕርሻ መሬት ለእግዚአብሔር ቢቀድስ፣ 23ካህኑ የዕርሻውን መሬት ዋጋ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ባለው ጊዜ መጠን ይተምናል፤ ሰውየው የተተመነውን ዋጋ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ አድርጎ በዚያ ዕለት ይክፈል። 24በኢዮቤልዩ ዓመትም የዕርሻው መሬት የቀድሞው ባለርስት ለነበረው፣ ለሸጠውም ሰው ይመለሳል። 25እያንዳንዱ ዋጋ የሚተመነው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ልክ ሆኖ አንዱ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው።
26“ ‘የእንስሳት በኵር ቀድሞውኑ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ፣ ማንም ሰው የእንስሳትን በኵር ለእግዚአብሔር መቀደስ አይችልም፤ በሬም#27፥26 የዕብራይስጡ ቃል ተባዕትና እንስትን ሊያጠቃልል ይችላል። ሆነ በግ የእግዚአብሔር ነውና። 27እንስሳው ርኩስ ከሆነ ግን፣ ባለቤቱ በተተመነው ዋጋ ላይ አንድ ዐምስተኛ ጨምሮ ሊዋጀው ይችላል፤ የማይዋጀው ከሆነ ግን በተተመነው ዋጋ ይሸጥ።
28“ ‘ነገር ግን ለእግዚአብሔር የተሰጠ፣ ማንኛውም ነገር ሰውም ሆነ እንስሳ ወይም በውርስ የተገኘ መሬት አይሸጥም፤ አይዋጅምም። ለእግዚአብሔር የተሰጠ ማንኛውም ነገር እጅግ የተቀደሰ ነውና።
29“ ‘እንዲጠፋ የተወሰነ ማንኛውም ሰው አይዋጅም፤ መገደል አለበት።
30“ ‘ከዕርሻ ምርትም ሆነ ከዛፍ ፍሬ፣ ማንኛውም ከምድሪቱ የሚገኝ ዐሥራት የእግዚአብሔር ነው፤ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ነው። 31አንድ ሰው ከዐሥራቱ የትኛውንም መዋጀት ቢፈልግ፣ በዋጋው ላይ አንድ ዐምስተኛ መጨመር አለበት። 32ከቀንድ ከብቶች፣ ከበጎችና ከፍየሎች መንጋ የሚወጣው ዐሥራት ከእረኛ በትር በታች ከሚያልፉት ዐሥረኛው እንስሳ ይሆናል፤ ይህም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው። 33ሰውየው መልካም የሆነውን መልካም ካልሆነው አይለይ ወይም አይተካ፤ አንዱን በሌላው ቢተካ ግን ሁለቱም እንስሳት የተቀደሱ ይሆናሉ፤ ሊዋጁም አይችሉም።’ ”
34 እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ በሙሴ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝብ የሰጣቸው ትእዛዞች እነዚህ ናቸው።

Currently Selected:

ዘሌዋውያን 27: NASV

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ