ዘኍልቍ 26
26
ሁለተኛው የሕዝብ ቈጠራ
1ከመቅሠፍቱ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴንና የካህኑን የአሮንን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፤ 2“ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን፣ በእስራኤልም ጦር ሰራዊት ውስጥ ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ሁሉ ከመላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ከየቤተ ሰቡ ቍጠሩ።” 3ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ#26፥3 በዕብራይስጥ የኢያሪኮ ዮርዳኖስ የሚባል ሲሆን፤ ይህም የዮርዳኖስ ወንዝ የጥንት ስም ሳይሆን አይቀርም። ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ ለሕዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤ 4“እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆነውን ቍጠሩ።”
ከግብጽ የወጡት እስራኤላውያንም እነዚህ ነበሩ፤
5የእስራኤል የበኵር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤
በሄኖኅ በኩል፣ የሄኖኀውያን ጐሣ፤
በፈሉስ በኩል፣ የፈሉሳውያን ጐሣ፤
6በአስሮን በኩል፣ የአስሮናውያን ጐሣ፤
በከርሚ በኩል፣ የከርማውያን ጐሣ፤
7እነዚህ የሮቤል ጐሣዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ ሦስት ሺሕ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።
8የፈሉስ ልጅ ኤልያብ ሲሆን፣ 9የኤልያብ ልጆች ደግሞ፣ ነሙኤል ዳታንና አቤሮን ነበሩ። እነዚሁ ዳታንና አቤሮን በሙሴና በአሮን ላይ ያመፁ የማኅበሩ ሹማምት ሲሆኑ፣ ቆሬና ተከታዮቹ በእግዚአብሔር ላይ ባመፁ ጊዜ እነርሱም በነገሩ ነበሩበት። 10ሁለት መቶ ዐምሳዎቹን ሰዎች እሳት በበላቻቸው ጊዜ የቆሬ ተከታዮች ሲሞቱ እነዚህን ደግሞ ምድር ተከፍታ ከርሱ ጋራ ዋጠቻቸው፤ መቀጣጫም ሆኑ፤ 11የቆሬ የዘር ሐረግ ግን አልጠፋም።
12የስምዖን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤
በነሙኤል በኩል፣ የነሙኤላውያን ጐሣ፤
በያሚን በኩል፣ የያሚናውያን ጐሣ፤
በያኪን በኩል፣ የያኪናውያን ጐሣ፤
13በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤
በሳኡል በኩል፣ የሳኡላውያን ጐሣ፤
14እነዚህ የስምዖን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩትም ሃያ ሁለት ሺሕ ሁለት መቶ ነበሩ።
15የጋድ ዘሮች በየጐሣዎቻቸው እነዚህ ነበሩ፤
በጽፎን በኩል፣ የጽፎናውያን ጐሣ፤
በሐጊ በኩል፣ የሐጋውያን ጐሣ፤
በሹኒ በኩል፣ የሹናውያን ጐሣ፤
16በኤስና በኩል፣ የኤስናናውያን ጐሣ፤
በዔሪ በኩል፣ የዔራውያን ጐሣ፤
17በአሮዲ#26፥17 በኦሪተ ሳምራውያኑ ቅጅ አሮዲ፤ በማሶሬቲክ ቅጅ አሮድ ተብሏል። በኩል፣ የአሮዳውያን ጐሣ፤
በአርኤሊ በኩል፣ የአርኤላውያን ጐሣ፤
18እነዚህ የጋድ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አርባ ሺሕ ዐምስት መቶ ነበሩ።
19ዔርና አውናን የይሁዳ ልጆች ነበሩ፤ ነገር ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል።
20የይሁዳ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤
በሴሎም በኩል፣ የሴሎማውያን ጐሣ፤
በፋሬስ በኩል፣ የፋሬሳውያን ጐሣ፤
በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤
21የፋሬስ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤
በኤስሮም በኩል፣ የኤስሮማውያን ጐሣ፤
በሐሙል በኩል፣ የሐሙላውያን ጐሣ፤
22እነዚህ የይሁዳ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሰባ ስድስት ሺሕ ዐምስት መቶ ነበሩ።
23የይሳኮር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤
በቶላ በኩል፣ የቶላውያን ጐሣ፣
በፉዋ በኩል፣ የፉዋውያን ጐሣ፣
24በያሱብ በኩል፣ የያሱባውያን ጐሣ፣
በሺምሮን በኩል፣ የሺምሮናውያን ጐሣ፤
25እነዚህ የይሳኮር ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ስድሳ አራት ሺሕ ሦስት መቶ ነበሩ።
26የዛብሎን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤
በሴሬድ በኩል፣ የሴሬዳውያን ጐሣ፤
በኤሎን በኩል፣ የኤሎናውያን ጐሣ፣
በያሕልኤል በኩል፣ የያሕልኤላውያን ጐሣ፤
27እነዚህ የዛብሎን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ስድሳ ሺሕ ዐምስት መቶ ነበሩ።
28የዮሴፍ ዘሮች በምናሴና በኤፍሬም በኩል ያሉት በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤
29የምናሴ ዘሮች፤
በማኪር በኩል፣ የማኪራውያን ጐሣ፤ ማኪርም የገለዓድ አባት ነው፤
በገለዓድ በኩል፣ የገለዓዳውያን ጐሣ፤
30የገለዓድ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤
በኢዔዝር በኩል፣ የኢዓዝራውያን ጐሣ፣
በኬሌግ በኩል፣ የኬሌጋውያን ጐሣ፣
31በአሥሪኤል በኩል፣ የአሥሪኤላውያን ጐሣ፣
በሴኬም በኩል፣ የሴኬማውያን ጐሣ፣
32በሸሚዳ በኩል፣ የሸሚዳውያን ጐሣ፣
በአፌር በኩል፣ የኦፌራውያን ጐሣ፣
33የአፌር ልጅ ሰለጰዓድ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጻ ይባላሉ።
34እነዚህ የምናሴ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ዐምሳ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ነበሩ።
35የኤፍሬም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤
በሱቱላ በኩል፣ የሱቱላውያን ጐሣ፣
በቤኬር በኩል፣ የቤኬራውያን ጐሣ፣
በታሐን በኩል፣ የታሐናውያን ጐሣ፤
36የሱቱላ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤
በዔዴን በኩል፣ የዔዴናውያን ጐሣ፤
37እነዚህ የኤፍሬም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺሕ ዐምስት መቶ ነበሩ።
እነዚህም በየጐሣቸው የተቈጠሩ የዮሴፍ ዘሮች ነበሩ።
38የብንያም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤
በቤላ በኩል፣ የቤላውያን ጐሣ፣
በአስቤል በኩል፣ የአስቤላውያን ጐሣ፣
በአኪራን በኩል፣ የአኪራናውያን ጐሣ፣
39በሶፋን#26፥39 ጥቂት የማሶሬቲክ፣ የኦሪተ ሳምራውያን፣ የቩልጌትና የሱርስት ቅጆች ሶፋን የሚሉ ሲሆን፣ አያሌ የማሶሬቲክ ቅጆች ግን ሼፉፋም ይላሉ። በኩል፣ የሶፋናውያን ጐሣ፣
በሑፋም በኩል፣ የሑፋማውያን ጐሣ፤
40የቤላ ዘሮች በአርድና በናዕማን በኩል፤
በአርድ በኩል፣ የአርዳውያን ጐሣ፣
በናዕማን በኩል፣ የናዕማናውያን ጐሣ፤
41እነዚህ የብንያም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ ዐምስት ሺሕ ስድስት መቶ ነበሩ።
42የዳን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤
በስምዔ በኩል፣ የሰምዔያውያን ጐሣዎች።
እነዚህ እንግዲህ የዳን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ 43ሁሉም የሰምዔያውያን ጐሣዎች ነበሩ፤ ከእነዚህ የተቈጠሩት ደግሞ ስድሳ አራት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ።
44የአሴር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤
በዪምና በኩል፣ የዪምናውያን ጐሣ፣
በየሱዊ በኩል፣ የየሱዋውያን ጐሣ፣
በበሪዓ በኩል፣ የበሪዓውያን ጐሣ፤
45እንዲሁም በበሪዓ ዘሮች በኩል፣
በሔቤር በኩል፣ የሔቤራውያን ጐሣ፣
በመልኪኤል በኩል፣ የመልኪኤላውያን ጐሣ።
46አሴር ሤራሕ የምትባል ልጅ ነበረችው።
47እነዚህ የአሴር ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ዐምሳ ሦስት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ።
48የንፍታሌም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤
በያሕጽኤል በኩል፣ የያሕጽኤላውያን ጐሣ፣
በጉኒ በኩል፣ የጉናውያን ጐሣ፣
49በዬጽር የዬጽራውያን ጐሣ፤ በሺሌም በኩል፣ የሺሌማውያን ጐሣ።
50እነዚህ የንፍታሌም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አርባ ዐምስት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ።
51በአጠቃላይ የእስራኤል ወንዶች ቍጥር ስድስት መቶ አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበር።
52 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 53“ምድሪቱ በስማቸው ቍጥር ልክ ተደልድላ በርስትነት ለእነርሱ ትሰጥ። 54በርከት ያለ ቍጥር ላለው ጐሣ ሰፋ ያለውን ርስት፣ አነስ ያለ ቍጥር ላለው ጐሣ ደግሞ አነስ ያለውን ስጥ፤ ርስቱንም እያንዳንዱ በዝርዝሩ ላይ በተመለከተው ቍጥር መሠረት ይረከባል። 55የመሬት ድልድሉም በዕጣ ይሁን፤ እያንዳንዱ የሚወርሰውም በየነገድ አባቶቹ ስም ይሆናል። 56እያንዳንዱም ርስት በትልልቆቹና በትንንሾቹ ነገዶች መካከል በዕጣ ይደለደላል።”
57በየጐሣቸው የተቈጠሩት ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤
በጌርሶን በኩል፣ የጌርሶናውያን ጐሣ፣
በቀዓት በኩል፣ የቀዓታውያን ጐሣ፣
በሜራሪ በኩል፣ የሜራራውያን ጐሣ፤
58እነዚህም ደግሞ የሌዊ ጐሣዎች ነበሩ፤
የሊብናውያን ጐሣ፣
የኬብሮናውያን ጐሣ፣
የሞሖላውያን ጐሣ፣
የሙሳውያን ጐሣ፣
የቆሬያውያን ጐሣ።
ቀዓት የእንበረም አባት ነበረ፤ 59የእንበረም ሚስቱ ዮካብድ ትባል ነበር፤ እርሷም በግብጽ አገር ከሌዋውያን የተወለደች የሌዊ ዘር ነበረች። ከእንበረምም አሮንን፣ ሙሴንና እኅታቸውን ማርያምን ወለደች። 60አሮንም የናዳብና የአብዩድ፣ የአልዓዛርና የኢታምር አባት ነበር። 61ነገር ግን ናዳብና አብዩድ ባልተፈቀደ እሳት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ስላቀረቡ ሞቱ።
62አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሌዋውያን ወንዶች ሁሉ ተቈጥረው ሃያ ሦስት ሺሕ ሆኑ፤ እነርሱም ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ ርስት ተካፋዮች ስላልነበሩ ዐብረዋቸው አልተቈጠሩም።
63ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ካለው ከሞዓብ ሜዳ ላይ የእስራኤልን ሕዝብ በቈጠሩበት ወቅት የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው። 64ሙሴና ካህኑ አሮን በሲና ምድረ በዳ እስራኤላውያንን በቈጠሩ ጊዜ ከእነዚህ ከተቈጠሩት መካከል አንዳቸውም አልነበሩም፤ 65ምክንያቱም በርግጥ በምድረ በዳ እንደሚሞቱ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ነግሯቸው ነበር፤ ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ የተረፈ ማንም ሰው አልነበረም።
Currently Selected:
ዘኍልቍ 26: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.