ዘኍልቍ 27
27
የሰለጰዓድ ሴት ልጆች
1የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ልጅ፣ የአፌር ልጅ፣ የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ጐሣዎች ነበሩ፤ ስማቸውም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጻ ይባላል። እነርሱም፣ 2ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ቀረቡ፤ በሙሴ፣ በካህኑ በአልዓዛር፣ በመሪዎችና በመላው ማኅበርም ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፤ 3“አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ ተባብረው በእግዚአብሔር ላይ ካመፁት ከቆሬ ተከታዮች ጋራ አልነበረም፤ የሞተው ግን በራሱ ኀጢአት ሲሆን፣ ወንዶች ልጆችም አልነበሩትም። 4ታዲያ አባታችን ወንድ ልጅ ባለመውለዱ ስሙ ከጐሣዎቹ ተለይቶ እንዴት ይጠፋል? ለእኛም በአባታችን ዘመዶች መካከል ርስት ስጡን።”
5ስለዚህ ሙሴ ጕዳያቸውን ወደ እግዚአብሔር አቀረበ፤ 6እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ 7“የሰለጰዓድ ልጆች ጥያቄ ትክክል ነው፤ በርግጥ በአባታቸው ዘመዶች መካከል ድርሻቸውን ርስት አድርገህ ልትሰጣቸው ስለሚገባ የአባታቸውን ድርሻ ለእነርሱ አስተላልፍላቸው።
8“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘አንድ ሰው ወንድ ልጅ ሳይተካ ቢሞት ውርሱን ለሴት ልጁ አስተላልፉ። 9ሴት ልጅ ከሌለችው ደግሞ ውርሱን ለወንድሞቹ ስጡ። 10ወንድሞች ከሌሉትም ውርሱን ለአባቱ ወንድሞች ስጡ። 11አባቱ፣ ወንድሞች ከሌሉት ውርሱን ከጐሣው መካከል ቅርብ ለሆነ ዘመዱ ይስጥ፤ እርሱም ይውረሰው። ይህም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤላውያን ሕጋዊ መመሪያ ይሆናቸዋል።’ ”
ኢያሱ በሙሴ እግር ተተካ
12ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በዓባሪም ሸንተረር ላይ ወዳለው ወደዚህ ተራራ ውጣና ለእስራኤላውያን የሰጠኋቸውን ምድር እይ። 13ካየኸውም በኋላ አንተም እንደ ወንድምህ እንደ አሮን ወደ ሕዝብህ ትሰበሰባለህ፤ 14ምክንያቱም ማኅበረ ሰቡ በጺን ምድረ በዳ ባለው ውሃ አጠገብ ባመፁ ጊዜ እኔን በሕዝቡ ፊት ቅዱስ አድርጋችሁ ለማክበር ሁለታችሁም ትእዛዜን ስላልጠበቃችሁ ነው።” ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ የሚገኝ የመሪባ ውሃ ነው።
15ሙሴ እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ 16“ሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆነ ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ማኅበረ ሰብ ላይ ሰው ይሹም፤ 17እርሱም፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ እረኛ እንደሌለው የበግ መንጋ እንዳይሆን በፊቱ የሚወጣና የሚገባ፣ መርቶ የሚያወጣውና የሚያገባው እንዲሆን ነው።”
18ስለዚህም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “መንፈስ ቅዱስ#27፥18 ወይም መንፈስ ያደረበትን የነዌን ልጅ ኢያሱን ወስደህ እጅህን ጫንበት። 19በካህኑ በአልዓዛርና በመላው ማኅበር ፊት እንዲቆም አድርገው፤ በፊታቸውም ሹመው፤ 20መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ እንዲታዘዝለትም ከሥልጣንህ ከፍለህ ስጠው። 21እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሆኖ በኡሪም በመጠየቅ ውሳኔ በሚያስገኝለት በካህኑ በአልዓዛር ፊት ይቆማል፤ እርሱም ሆነ መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ በአልዓዛር ትእዛዝ ይወጣሉ፤ በርሱም ቃል ይገባሉ።”
22ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ኢያሱንም ወስዶ በካህኑ በአልዓዛርና በመላው የእስራኤል ማኅበር ፊት አቆመው፤ 23ከዚያም እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘው መሠረት እጁን በራሱ ላይ ጭኖ ሾመው።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.