የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 11

11
መዝሙር 11
ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር ታምኛለሁ፤
ታዲያ ነፍሴን፣ “እንደ ወፍ ወደ ተራራ ብረሪ”
ለምን ትሏታላችሁ?
2ደግሞም ለምን እንዲህ ትሉኛላችሁ?
“ክፉዎች፣ እነሆ፤ ቀስታቸውን ገትረዋል፤
የቅኑን ሰው ልብ በጨለማ ለመንደፍ፣
ፍላጻቸውን በአውታሩ ላይ ደግነዋል።
3መሠረቱ ከተናደ፣
ጻድቅ ምን ማድረግ ይችላል?”#11፥3 ወይም ጻድቁ ምን እያደረገ ነው?
4 እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤
እግዚአብሔር ዙፋን በሰማይ ነው።
ዐይኖቹ ሰዎችን ይመለከታሉ፤
ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
5 እግዚአብሔር ጻድቁንና ክፉውን ይመረምራል፤#11፥5 ወይም ጻድቁ እግዚአብሔር ኀጥኡን ይመረምራል
ዐመፃን የሚወድዱትን ግን፣
ነፍሱ ትጠላቸዋለች።
6እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤
የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣
የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው።
7 እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፤
የጽድቅ ሥራም ይወድዳል፤
ቅኖችም ፊቱን ያያሉ።

Currently Selected:

መዝሙር 11: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ