የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 12

12
መዝሙር 12
ለመዘምራን አለቃ፤ በሸሚኒት#12፥0 በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም። የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር።
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ደግ ሰው የለምና አንተው ድረስልኝ!
ከሰዎችም መካከል አንድ ታማኝ አይገኝም።
2እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤
በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራሉ።
3ሸንጋዩን ከንፈር ሁሉ፣
ነገር የምታበዛውንም ምላስ እግዚአብሔር ያጥፋ!
4እነዚህም፣ “በአንደበታችን እንረታለን፤
ከንፈራችን የእኛ ነው፤#12፥4 ወይም ከንፈራችን ማረሻ ምላጫችን ነው ጌታችንስ ማነው?”
የሚሉ ናቸው።
5 እግዚአብሔር፣ “ስለ ችግረኞች መከራ፣
ስለ ድኾችም ጩኸት፣
አሁን እነሣለሁ፤
በናፈቁትም ሰላም አኖራቸዋለሁ” ይላል።
6እግዚአብሔር ቃል የጠራ ቃል ነው፤
ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ፣
በምድር ላይ በከውር እንደ ተፈተነ ብር ነው።
7 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ትጠብቀናለህ፤
ከዚህም ትውልድ ለዘላለም ትከልለናለህ።
8በሰዎች ዘንድ ክፋት ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ፣
ዐመፀኞች በየአቅጣጫው በዛቻ ይዞራሉ።

Currently Selected:

መዝሙር 12: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ