መዝሙር 126

126
መዝሙር 126
መዝሙረ መዓርግ።
1 እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ#126፥1 ወይም እግዚአብሔር ሀብቷን ይመልሳል። በመለሰ ጊዜ፣
ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም።#126፥1 ወይም የሰዎቿ ጤንነት ይታደሳል።
2በዚያ ጊዜ አፋችን በሣቅ፣
አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤
በዚያ ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣
እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ።
3 እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤
እኛም ደስ አለን።
4 እግዚአብሔር ሆይ፤ በኔጌብ እንዳሉ ጅረቶች፣
ምርኳችንን መልስ።#126፥4 ወይም ሀብታችንን መልስ
5በእንባ የሚዘሩ፣
በእልልታ ያጭዳሉ።
6ዘር ቋጥረው፣
እያለቀሱ የተሰማሩ፣
ነዷቸውን ተሸክመው፣
እልል እያሉ ይመለሳሉ።

Currently Selected:

መዝሙር 126: NASV

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ