መዝሙር 131

131
መዝሙር 131
የዳዊት መዝሙረ መዓርግ።
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ልቤ አልታበየም፤
ዐይኔ ከፍ ከፍ አላለም፤
ሐሳቤ ለዐጕል ትልቅነት አልተነሣሣም፤
ከዐቅሜም በላይ አልተንጠራራሁም።
2ነገር ግን ነፍሴን ጸጥ፣ ዝም አሠኘኋት፤
ጡት የጣለ ልጅ ዐርፎ እናቱ ላይ እንደሚቀመጥ፣
ነፍሴ ጡት እንዳስተዉት ሕፃን በውስጤ ጸጥ አለች።
3እስራኤል ሆይ፤ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣
በእግዚአብሔር ተስፋ አድርግ።

Currently Selected:

መዝሙር 131: NASV

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ