መዝሙር 134
134
መዝሙር 134
መዝሙረ መዓርግ።
1እናንተ በሌሊት ቆማችሁ በእግዚአብሔር ቤት የምታገለግሉ፣
የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ እግዚአብሔርን ባርኩ።
2በመቅደሱ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፤
እግዚአብሔርንም ባርኩ።
3ሰማይንና ምድርን የሠራ እግዚአብሔር፣
ከጽዮን ይባርክህ።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.