መዝሙር 14
14
መዝሙር 14
14፥1-7 ተጓ ምብ – መዝ 53፥1-6
ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር።
1ሞኝ#14፥1 በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ ሞኝ ወይም ተላላ ተብለው የተተረጐሙት የዕብራይስጥ ቃላት ግብረ ገባዊ ንቅዘትን የሚያመለክቱ ናቸው። በልቡ፣
“እግዚአብሔር የለም” ይላል።
ብልሹዎች ናቸው፤ ጸያፍ ነገሮችን ይሠራሉ።
በጎ ነገር የሚሠራ አንድ እንኳን የለም።
2የሚያስተውል፣ እግዚአብሔርን የሚፈልግ እንዳለ ለማየት፣
እግዚአብሔር ከሰማይ ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ።
3ሁሉም ወደ ሌላ ዘወር አሉ፤
በአንድነትም ተበላሹ፤
መልካም የሚያደርግ የለም፤
አንድ እንኳ።
4ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉት፣
እግዚአብሔርንም የማይጠሩት፣
እነዚህ ክፉ አድራጊዎች ምንም አያውቁምን?
5ባሉበት ድንጋጤ ውጧቸዋል፤
እግዚአብሔር በጻድቃን መካከል ይገኛልና።
6እናንተ የድኾችን ዕቅድ ለማፋለስ ትሻላችሁ፤
እግዚአብሔር ግን መጠጊያቸው ነው።
7ምነው ለእስራኤል የሚሆን መዳን ከጽዮን በወጣ!
እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፣
ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤልም ሐሤት ያድርግ።
Currently Selected:
መዝሙር 14: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.