መዝሙር 22
22
መዝሙር 22
ለመዘምራን አለቃ፤ “በንጋት አጋዘን” ዜማ የሚዜም፤ የዳዊት መዝሙር።
1አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?
እኔን ከማዳን፣
ከመቃተቴም ቃል ለምን ራቅህ?
2አምላኬ ሆይ፤ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤
አንተ ግን አልመለስህልኝም፤
በሌሊት እንኳ አላረፍሁም።
3አንተ ግን ቅዱሱ ነጋሢ፤#22፥3 ወይም አንተ ግን ቅዱስ ነህ፤ በእስራኤል ምስጋና ላይ በዙፋን ተቀምጠሃል
የእስራኤልም ምስጋና ነህ።
4አባቶቻችን በአንተ ታመኑ፤
ተማመኑብህ፤ አንተም ታደግሃቸው።
5ወደ አንተ ጮኹ፤ ዳኑም፤
በአንተም ታመኑ፤ አላፈሩም።
6እኔ ግን ትል እንጂ ሰው አይደለሁም፤
ሰው ያላገጠብኝ፣ ሕዝብም የናቀኝ ነኝ።
7የሚያዩኝ ሁሉ ይሣለቁብኛል፤
ራሳቸውንም እየነቀነቁ እንዲህ እያሉ ይዘልፉኛል፤
8“በእግዚአብሔር ተማምኗል፤
እንግዲህ እርሱ ያድነው፤
ደስ የተሠኘበትን፣
እስኪ ይታደገው።”
9አንተ ግን ከማሕፀን አወጣኸኝ፤
በእናቴም ጡት ሳለሁ፣ መታመኛ ሆንኸኝ።
10ከማሕፀን ስወጣም በአንተ ላይ ተጣልሁ፤
ከእናቴ ሆድ ጀምሮም አንተ አምላኬ ነህ።
11መከራ እየተቃረበ ነውና፣
የሚረዳኝም የለምና፣
ከእኔ አትራቅ።
12ብዙ ኰርማዎች ከበቡኝ፤
ኀይለኛ የባሳን በሬዎችም ዙሪያዬን ቆሙ።
13እንደሚነጥቅና እንደሚያገሣ አንበሳ፣
አፋቸውን ከፈቱብኝ።
14እንደ ውሃ ፈሰስሁ፤
ዐጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ፤
ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤
በውስጤም ቀለጠ።
15ጕልበቴ እንደ ገል ደረቀ፤
ምላሴ ከላንቃዬ ጋራ ተጣበቀ፤
ወደ ሞት ዐፈርም አወረድኸኝ።#22፥15 ወይም …ዐፈር ውስጥ ተኛሁኝ
16ውሾች ከበቡኝ፤
የክፉዎች ሸንጎ በዙሪያዬ ተሰልፏል፤
እጆቼንና እግሮቼንም ቸነከሩኝ።#22፥16 አንዳንድ የዕብራይስጥ የጥንት ቅጆች፣ ሰብዓ ሊቃናትና ሱርስት እንዲሁ ሲሆኑ፣ አብዛኛዎቹ የዕብራይስጥ የጥንት ቅጆች እንደ አንበሳ ይላሉ።
17ዐጥንቶቼን ሁሉ አንድ በአንድ መቍጠር እችላለሁ፤
እነርሱም አፍጥጠው ይመለከቱኛል።
18ልብሶቼን ተከፋፈሉ፤
በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።
19አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤
ዐጋዤ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
20ነፍሴን ከሰይፍ ታደጋት፤
ውድ ሕይወቴንም ከውሾች ጡጫ አድናት።
21ከአንበሶች አፍ አድነኝ፤
ከአውራሪስ ቀንድም ታደገኝ።#22፥21 ወይም ሰምተኸኛል
22ስምህን ለወንድሞቼ ዐውጃለሁ፤
በጉባኤም መካከል አወድስሃለሁ።
23እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ፤ አወድሱት፤
እናንተ የያዕቆብ ዘር ሁላችሁ፤ አክብሩት፤
የእስራኤልም ዘር ሁላችሁ፤ እርሱን ፍሩት።
24እርሱ የተጨነቀውን ሰው ጭንቀት፣
አልናቀም፤ ቸልም አላለምና፤
ፊቱንም ከርሱ አልሰወረም፤
ነገር ግን ድረስልኝ ብሎ ሲጮኽ ሰማው።
25በታላቅ ጉባኤ የማቀርበው ምስጋናዬ ከአንተ የመጣ ነው፤
እርሱን በሚፈሩት#22፥25 ዕብራይስጡ እኔ በሚፈሩኝ ይላል። ፊት ስእለቴን እፈጽማለሁ።
26ምስኪኖች በልተው ይጠግባሉ፤
እግዚአብሔርን የሚሹትም ያመሰግኑታል፤
ልባችሁም ለዘላለም ሕያው ይሁን!
27የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስታውሳሉ፤
ወደ እግዚአብሔርም ይመለሳሉ፤
የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ፣
በፊቱ ይሰግዳሉ።
28መንግሥት የእግዚአብሔር ናትና፤
ሕዝቦችንም የሚገዛ እርሱ ነው።
29የምድር ከበርቴዎች ይበላሉ፤
ይሰግዱለታልም፤
ነፍሱን በሕይወት ማቈየት የማይችለው፣ ወደ ዐፈር
ተመላሽ የሆነው ሁሉ በፊቱ ይንበረከካል።
30የኋለኛው ትውልድ ያገለግለዋል፤
ለመጪው ትውልድ ስለ ጌታ ይነገረዋል።
31ገና ላልተወለደ ሕዝብ፣
ጽድቁን ይነግራሉ፤
እርሱ ይህን አድርጓልና።
Currently Selected:
መዝሙር 22: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
መዝሙር 22
22
መዝሙር 22
ለመዘምራን አለቃ፤ “በንጋት አጋዘን” ዜማ የሚዜም፤ የዳዊት መዝሙር።
1አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?
እኔን ከማዳን፣
ከመቃተቴም ቃል ለምን ራቅህ?
2አምላኬ ሆይ፤ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤
አንተ ግን አልመለስህልኝም፤
በሌሊት እንኳ አላረፍሁም።
3አንተ ግን ቅዱሱ ነጋሢ፤#22፥3 ወይም አንተ ግን ቅዱስ ነህ፤ በእስራኤል ምስጋና ላይ በዙፋን ተቀምጠሃል
የእስራኤልም ምስጋና ነህ።
4አባቶቻችን በአንተ ታመኑ፤
ተማመኑብህ፤ አንተም ታደግሃቸው።
5ወደ አንተ ጮኹ፤ ዳኑም፤
በአንተም ታመኑ፤ አላፈሩም።
6እኔ ግን ትል እንጂ ሰው አይደለሁም፤
ሰው ያላገጠብኝ፣ ሕዝብም የናቀኝ ነኝ።
7የሚያዩኝ ሁሉ ይሣለቁብኛል፤
ራሳቸውንም እየነቀነቁ እንዲህ እያሉ ይዘልፉኛል፤
8“በእግዚአብሔር ተማምኗል፤
እንግዲህ እርሱ ያድነው፤
ደስ የተሠኘበትን፣
እስኪ ይታደገው።”
9አንተ ግን ከማሕፀን አወጣኸኝ፤
በእናቴም ጡት ሳለሁ፣ መታመኛ ሆንኸኝ።
10ከማሕፀን ስወጣም በአንተ ላይ ተጣልሁ፤
ከእናቴ ሆድ ጀምሮም አንተ አምላኬ ነህ።
11መከራ እየተቃረበ ነውና፣
የሚረዳኝም የለምና፣
ከእኔ አትራቅ።
12ብዙ ኰርማዎች ከበቡኝ፤
ኀይለኛ የባሳን በሬዎችም ዙሪያዬን ቆሙ።
13እንደሚነጥቅና እንደሚያገሣ አንበሳ፣
አፋቸውን ከፈቱብኝ።
14እንደ ውሃ ፈሰስሁ፤
ዐጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ፤
ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤
በውስጤም ቀለጠ።
15ጕልበቴ እንደ ገል ደረቀ፤
ምላሴ ከላንቃዬ ጋራ ተጣበቀ፤
ወደ ሞት ዐፈርም አወረድኸኝ።#22፥15 ወይም …ዐፈር ውስጥ ተኛሁኝ
16ውሾች ከበቡኝ፤
የክፉዎች ሸንጎ በዙሪያዬ ተሰልፏል፤
እጆቼንና እግሮቼንም ቸነከሩኝ።#22፥16 አንዳንድ የዕብራይስጥ የጥንት ቅጆች፣ ሰብዓ ሊቃናትና ሱርስት እንዲሁ ሲሆኑ፣ አብዛኛዎቹ የዕብራይስጥ የጥንት ቅጆች እንደ አንበሳ ይላሉ።
17ዐጥንቶቼን ሁሉ አንድ በአንድ መቍጠር እችላለሁ፤
እነርሱም አፍጥጠው ይመለከቱኛል።
18ልብሶቼን ተከፋፈሉ፤
በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።
19አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤
ዐጋዤ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
20ነፍሴን ከሰይፍ ታደጋት፤
ውድ ሕይወቴንም ከውሾች ጡጫ አድናት።
21ከአንበሶች አፍ አድነኝ፤
ከአውራሪስ ቀንድም ታደገኝ።#22፥21 ወይም ሰምተኸኛል
22ስምህን ለወንድሞቼ ዐውጃለሁ፤
በጉባኤም መካከል አወድስሃለሁ።
23እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ፤ አወድሱት፤
እናንተ የያዕቆብ ዘር ሁላችሁ፤ አክብሩት፤
የእስራኤልም ዘር ሁላችሁ፤ እርሱን ፍሩት።
24እርሱ የተጨነቀውን ሰው ጭንቀት፣
አልናቀም፤ ቸልም አላለምና፤
ፊቱንም ከርሱ አልሰወረም፤
ነገር ግን ድረስልኝ ብሎ ሲጮኽ ሰማው።
25በታላቅ ጉባኤ የማቀርበው ምስጋናዬ ከአንተ የመጣ ነው፤
እርሱን በሚፈሩት#22፥25 ዕብራይስጡ እኔ በሚፈሩኝ ይላል። ፊት ስእለቴን እፈጽማለሁ።
26ምስኪኖች በልተው ይጠግባሉ፤
እግዚአብሔርን የሚሹትም ያመሰግኑታል፤
ልባችሁም ለዘላለም ሕያው ይሁን!
27የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስታውሳሉ፤
ወደ እግዚአብሔርም ይመለሳሉ፤
የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ፣
በፊቱ ይሰግዳሉ።
28መንግሥት የእግዚአብሔር ናትና፤
ሕዝቦችንም የሚገዛ እርሱ ነው።
29የምድር ከበርቴዎች ይበላሉ፤
ይሰግዱለታልም፤
ነፍሱን በሕይወት ማቈየት የማይችለው፣ ወደ ዐፈር
ተመላሽ የሆነው ሁሉ በፊቱ ይንበረከካል።
30የኋለኛው ትውልድ ያገለግለዋል፤
ለመጪው ትውልድ ስለ ጌታ ይነገረዋል።
31ገና ላልተወለደ ሕዝብ፣
ጽድቁን ይነግራሉ፤
እርሱ ይህን አድርጓልና።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.