የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 23

23
መዝሙር 23
የዳዊት መዝሙር።
1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፤
አንዳች አይጐድልብኝም።
2በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል፤
በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል፤
3ነፍሴንም ይመልሳታል።
ስለ ስሙም፣
በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።
4በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ#23፥4 ወይም እጅግ ጨለማ በሆነው ሸለቆ ውስጥ
ብሄድ እንኳ፣
አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንህ፣
ክፉን አልፈራም፤
በትርህና ምርኵዝህ፣
እነርሱ ያጽናኑኛል።
5ጠላቶቼ እያዩ፣
በፊቴ ማእድ አዘጋጀህልኝ፤
ራሴን በዘይት ቀባህ፤
ጽዋዬም ሞልቶ ይፈስሳል።
6በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣
በጎነትና ምሕረት በርግጥ ይከተሉኛል፤
እኔም በእግዚአብሔር ቤት፣
ለዘላለም እኖራለሁ።

Currently Selected:

መዝሙር 23: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ