የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 26

26
መዝሙር 26
የዳዊት መዝሙር።
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ነቀፋ እንደ መሆኔ፣
አንተው ፍረድልኝ።
ወዲያ ወዲህ ሳልልም፣
እግዚአብሔር ታምኛለሁ።
2 እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈትነኝ፤ መርምረኝም፤
ልቤንና ውስጤን መርምር፤
3ምሕረትህ ከፊቴ አልተለየምና፣
በእውነትህም ተመላለስሁ።
4ከማይረቡ ጋራ አልተቀመጥሁም፤
ከግብዞችም ጋራ አልተባበርሁም።
5የክፉዎችን ማኅበር ተጸየፍሁ፤
ከዐመፀኞችም ጋራ አልቀመጥም።
6እጆቼን በየዋህነት እታጠባለሁ፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ መሠዊያህንም እዞራለሁ፤
7የምስጋናን ድምፅ አሰማ ዘንድ፣
ታምራትህንም አወራ ዘንድ ነው።
8 እግዚአብሔር ሆይ፤ የምትኖርበትን ቤት፣
የክብርህን ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።
9ነፍሴን ከኀጢአተኞች ጋራ፣
ሕይወቴንም ከደም አፍሳሾች ጋራ አታስወግዳት።
10በእነርሱ እጅ የተንኰል ዕቅድ አለ፤
ቀኝ እጃቸውም ጕቦን ያጋብሳል።
11እኔ ግን በተአማኒ ሕይወት እጓዛለሁ፤
አድነኝ፤ ምሕረትንም አድርግልኝ።
12እግሮቼ በደልዳላ ስፍራ ቆመዋል፤
በታላቅ ጉባኤ መካከልም እግዚአብሔርን እባርከዋለሁ።

Currently Selected:

መዝሙር 26: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ