የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 53

53
መዝሙር 53
53፥1-6 ተጓ ምብ – መዝ 14፥1-7
ለመዘምራን አለቃ፤ በማኸላት፤#53 ርእስ በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም። የዳዊት ማስኪል።#53 ርእስ በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም።
1ሞኝ በልቡ፣
“እግዚአብሔር የለም” ይላል።
ብልሹዎች ናቸው፤ ተግባራቸውም ጸያፍ ነው፤
በጎ ነገር የሚሠራ አንድ እንኳን የለም።
2የሚያስተውል፣
እግዚአብሔርን የሚፈልግ እንዳለ ለማየት፣
እግዚአብሔር ከሰማይ
ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ።
3ሁሉም ወደ ሌላ ዘወር አሉ፤
በአንድነትም ተበላሹ፤
መልካም የሚያደርግ የለም፤
አንድ እንኳ።
4ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉት፣
እግዚአብሔርንም የማይጠሩት፣
እነዚህ ክፉ አድራጊዎች ምንም አያውቁምን?
5የሚያስፈራ ነገር በሌለበት፣
በዚያ፣ ድንጋጤ ውጧቸዋል፤
እግዚአብሔር የዘመቱብህን ሰዎች ዐጥንት በተነ፤
እርሱ እግዚአብሔር ስለ ናቃቸው፣ አንተ አሳፈርሃቸው።
6ምነው ለእስራኤል የሚሆን መዳን ከጽዮን በወጣ!
እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፣
ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤልም ሐሤት ያድርግ።

Currently Selected:

መዝሙር 53: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ