የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 62

62
መዝሙር 62
ለመዘምራን አለቃ፤ ለኤዶታም፤ የዳዊት መዝሙር።
1ነፍሴ ዕረፍት የምታገኘው በእግዚአብሔር ብቻ ነው፤
ድነቴም የሚመጣልኝ ከርሱ ዘንድ ነው።
2ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤
መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም።
3ሰውን የምታጠቁት እስከ መቼ ነው?
ይህን የዘመመ ግድግዳ፣ የተንጋደደ ዐጥር፣
ሁላችሁ ገፍታችሁ ልትጥሉት ትሻላችሁ?
4ከታላቅ ክብሩ ሊያዋርዱት፣
ይህን አንድ ነገር ወጠኑ፤
ሐሰት ባለበት ነገር ደስ ይሰኛሉ፤
በአፋቸው ይመርቃሉ፤
በልባቸው ግን ይራገማሉ። ሴላ
5ነፍሴ ሆይ፤ ዐርፈሽ እግዚአብሔርን ብቻ ጠብቂ፤
ተስፋዬ ከርሱ ዘንድ ነውና።
6ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤
መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ እኔም አልናወጥም።
7መዳኔና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤#62፥7 ወይም ልዑል እግዚአብሔር ድነቴና ክብሬ ነው ተብሎ መተርጐም ይችላል።
ብርቱ ዐለቴና መሸሸጊያዬ በእግዚአብሔር ነው።
8ሰዎች ሆይ፤ ሁልጊዜ በርሱ ታመኑ፤
ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ፤
እግዚአብሔር መጠጊያችን ነውና። ሴላ
9ከተናቀ ወገን መወለድ ከንቱ፣
ከከበረውም መወለድ ሐሰት ነው።
በሚዛን ቢመዘኑ፣
የሰው ልጆች ሁሉ በአንድነት ከነፋስ የቀለሉ ናቸው።
10በዝርፊያ አትታመኑ፤
በቅሚያም ተስፋ አታድርጉ፤
በዚህ ብትበለጽጉም፣
ልባችሁ ይህን አለኝታ አያድርግ።
11እግዚአብሔር አንድ ነገር ተናገረ፤
እኔም ይህን ሁለት ጊዜ ሰማሁ፤
ኀይል የእግዚአብሔር ነው።
12ጌታ ሆይ፤ ምሕረትም የአንተ ነው፤
አንተ ለእያንዳንዱ፣
እንደ ሥራው ትከፍለዋለህ።

Currently Selected:

መዝሙር 62: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ