መዝሙር 70

70
መዝሙር 70
70፥1-5 ተጓ ምብ – መዝ 40፥13-17
ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር፤ ለመታሰቢያ።
1አምላክ ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ዘንበል በል፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
2ነፍሴን ለመንጠቅ የሚፈልጉ፣
ይፈሩ፤ ይዋረዱም፤ ጕዳቴንም የሚሹ፣
ተዋርደው በመጡበት ይመለሱ።
3በእኔ ላይ፣ “ዕሠይ! ዕሠይ!” የሚሉ፣
ተሸማቅቀው ወደ ኋላ ይመለሱ።
4አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ግን፣
ሐሤት ያድርጉ፤ በአንተም ደስም ይበላቸው፤
ማዳንህን የሚወድዱ ሁሉ ሁልጊዜ
“እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይበል!” ይበሉ።
5እኔ ግን ችግረኛና ድኻ ነኝ፤
አምላክ ሆይ፤ ፈጥነህ ድረስልኝ፤
አንተ ረዳቴና፣ ታዳጊዬም ነህና፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ አትዘግይ።

Currently Selected:

መዝሙር 70: NASV

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ