መዝሙር 93

93
መዝሙር 93
1 እግዚአብሔር ነገሠ፤ ግርማንም ተጐናጸፈ፤
እግዚአብሔር ግርማን ለበሰ፤
ብርታትንም ታጠቀ፤
ዓለም እንዳትናወጥ ጸንታለች፤
ማንም አይነቀንቃትም።
2ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤
አንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ።
3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ወንዞች ከፍ አደረጉ፤
ወንዞች ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ፤
ወንዞች የሚያስገመግም ማዕበላቸውን ከፍ አደረጉ።
4ከብዙ ውሆች ድምፅ ይልቅ፣
ከባሕርም ሞገድ ይልቅ፣
ከፍ ብሎ ያለው እግዚአብሔር ኀያል ነው።
5ምስክርነትህ የጸና ነው፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከ ዘላለሙ፣
ቤትህ በቅድስና ይዋባል።

Currently Selected:

መዝሙር 93: NASV

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ