መዝሙር 94
94
መዝሙር 94
1የበቀል አምላክ፣ አንተ እግዚአብሔር ሆይ፤
የበቀል አምላክ ሆይ፤ ደምቀህ ተገለጥ።
2አንተ የምድር ዳኛ ሆይ፤ ተነሥ፤
ለትዕቢተኞች የእጃቸውን ስጣቸው።
3ክፉዎች እስከ መቼ እግዚአብሔር ሆይ፤
ክፉዎች እስከ መቼ ይፈነጫሉ?
4የእብሪት ቃላት ያዥጐደጕዳሉ፤
ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ጕራ ይነዛሉ።
5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህን አደቀቁ፤
ርስትህንም አስጨነቁ።
6መበለቲቱንና መጻተኛውን ገደሉ፤
የድኻ አደጉንም ነፍስ አጠፉ።
7እነርሱም “እግዚአብሔር አያይም፤
የያዕቆብም አምላክ አያስተውልም” አሉ።
8እናንተ በሕዝቡ መካከል ያላችሁ ደነዞች፤ ልብ በሉ፤
እናንተ ሞኞች፤ ጥበበኞች የምትሆኑት መቼ ነው?
9ጆሮን የተከለው እርሱ አይሰማምን? ዐይንንስ የሠራ እርሱ አያይምን?
10ሕዝቦችን በተግሣጽ ወደ መንገድ የሚመልስ፣
ዕውቀትንስ ለሰው ልጆች የሚያስተምር አይቀጣምን?
11 እግዚአብሔር የሰው ሐሳብ
ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል።
12ብፁዕ ነው፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የምትገሥጸው፣
ከሕግህም የምታስተምረው ሰው፤
13ለኀጢአተኞች ጕድጓድ እስኪማስላቸው ድረስ፣
እርሱን ከመከራ ታሳርፈዋለህ።
14 እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥልምና፤
ርስቱንም አይተውም።
15ፍርድ ተመልሶ በጽድቅ አሠራር ላይ ይመሠረታል፤
ልባቸውም ቀና የሆነ ሁሉ ይከተሉታል።
16ክፉዎችን የሚቋቋምልኝ ማን ነው?
ከክፉ አድራጊዎችስ ጋራ የሚሟገትልኝ ማን ነው?
17 እግዚአብሔር ረዳቴ ባይሆን ኖሮ፣
ነፍሴ ወደ ዝምታው ዓለም ፈጥና በወረደች ነበር።
18እኔ፣ “እግሬ አዳለጠኝ” ባልሁ ጊዜ፣
እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ደግፎ ያዘኝ።
19የውስጤ ጭንቀት በበዛ መጠን፣
ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት።
20ዐመፃን ሕጋዊ የሚያደርግ፣
የጥፋት ዙፋን ከአንተ ጋራ ሊያብር ይችላልን?
21በጻድቁ ላይ ተሰልፈው ይወጣሉ፤
በንጹሑም ላይ ሞት ይፈርዳሉ።
22ለእኔ ግን እግዚአብሔር ምሽግ፣
አምላኬም መጠጊያ ዐለት ሆኖኛል።
23በደላቸውን ወደ ራሳቸው ይመልሳል፤
በክፋታቸውም ያጠፋቸዋል፤
እግዚአብሔር አምላካችን ይደመስሳቸዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
መዝሙር 94
94
መዝሙር 94
1የበቀል አምላክ፣ አንተ እግዚአብሔር ሆይ፤
የበቀል አምላክ ሆይ፤ ደምቀህ ተገለጥ።
2አንተ የምድር ዳኛ ሆይ፤ ተነሥ፤
ለትዕቢተኞች የእጃቸውን ስጣቸው።
3ክፉዎች እስከ መቼ እግዚአብሔር ሆይ፤
ክፉዎች እስከ መቼ ይፈነጫሉ?
4የእብሪት ቃላት ያዥጐደጕዳሉ፤
ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ጕራ ይነዛሉ።
5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህን አደቀቁ፤
ርስትህንም አስጨነቁ።
6መበለቲቱንና መጻተኛውን ገደሉ፤
የድኻ አደጉንም ነፍስ አጠፉ።
7እነርሱም “እግዚአብሔር አያይም፤
የያዕቆብም አምላክ አያስተውልም” አሉ።
8እናንተ በሕዝቡ መካከል ያላችሁ ደነዞች፤ ልብ በሉ፤
እናንተ ሞኞች፤ ጥበበኞች የምትሆኑት መቼ ነው?
9ጆሮን የተከለው እርሱ አይሰማምን? ዐይንንስ የሠራ እርሱ አያይምን?
10ሕዝቦችን በተግሣጽ ወደ መንገድ የሚመልስ፣
ዕውቀትንስ ለሰው ልጆች የሚያስተምር አይቀጣምን?
11 እግዚአብሔር የሰው ሐሳብ
ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል።
12ብፁዕ ነው፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የምትገሥጸው፣
ከሕግህም የምታስተምረው ሰው፤
13ለኀጢአተኞች ጕድጓድ እስኪማስላቸው ድረስ፣
እርሱን ከመከራ ታሳርፈዋለህ።
14 እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥልምና፤
ርስቱንም አይተውም።
15ፍርድ ተመልሶ በጽድቅ አሠራር ላይ ይመሠረታል፤
ልባቸውም ቀና የሆነ ሁሉ ይከተሉታል።
16ክፉዎችን የሚቋቋምልኝ ማን ነው?
ከክፉ አድራጊዎችስ ጋራ የሚሟገትልኝ ማን ነው?
17 እግዚአብሔር ረዳቴ ባይሆን ኖሮ፣
ነፍሴ ወደ ዝምታው ዓለም ፈጥና በወረደች ነበር።
18እኔ፣ “እግሬ አዳለጠኝ” ባልሁ ጊዜ፣
እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ደግፎ ያዘኝ።
19የውስጤ ጭንቀት በበዛ መጠን፣
ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት።
20ዐመፃን ሕጋዊ የሚያደርግ፣
የጥፋት ዙፋን ከአንተ ጋራ ሊያብር ይችላልን?
21በጻድቁ ላይ ተሰልፈው ይወጣሉ፤
በንጹሑም ላይ ሞት ይፈርዳሉ።
22ለእኔ ግን እግዚአብሔር ምሽግ፣
አምላኬም መጠጊያ ዐለት ሆኖኛል።
23በደላቸውን ወደ ራሳቸው ይመልሳል፤
በክፋታቸውም ያጠፋቸዋል፤
እግዚአብሔር አምላካችን ይደመስሳቸዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.