የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ማሕልየ መሓልይ 3

3
1ሌሊቱን ሙሉ በዐልጋዬ ላይ ሆኜ፣
ውዴን ተመኘሁ፤
ተመኘሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።
2ተነሥቼ ወደ ከተማዪቱ እወጣለሁ፤
በዋና ዋና መንገዶችና በአደባባዮች እዘዋወራለሁ፤
ውዴንም እፈልገዋለሁ፤
ስለዚህም ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።
3በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ፣
የከተማዪቱ ጠባቂዎች አገኙኝ፤
እኔም፣ “ውዴን አይታችኋል?”
አልኋቸው።
4ከእነርሱ ጥቂት ዕልፍ እንዳልሁ፣
ውዴን አገኘሁት፤ ያዝሁት፤
ወደ እናቴ ቤት እስካመጣው፣
በማሕፀን ወደ ተሸከመችኝም ዕልፍኝ
እስካገባው ድረስ አልለቀውም።
5እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤
ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣
ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት፣
በሚዳቋና በሜዳ ዋሊያ አማፅናችኋለሁ።
6ከከርቤና ከዕጣን፣
ከነጋዴም ቅመማ ቅመም ሁሉ በተዘጋጀ ሽቱ፣
መዐዛዋ የሚያውድ፣
እንደ ጢስ ዐምድ ከምድረ በዳ የምትወጣው ይህች ማን ናት?
7እነሆ፤ የሰሎሞን ሠረገላ
በታዋቂዎቹ የእስራኤል መኳንንት፣
ስድሳ ጦረኞች ታጅባለች፤
8ሁሉም ሰይፍ የታጠቁ፣
ሁሉም በጦርነት የተፈተኑ ናቸው፤
የሌሊት አደጋን ለመከላከልም፣
እያንዳንዳቸው ሰይፋቸውን በወገባቸው ታጥቀዋል።
9ንጉሥ ሰሎሞን የራሱን ሠረገላ ሠራ፤
የሠራውም ከሊባኖስ በመጣ ዕንጨት ነው።
10ምሰሶዎቹን ከብር፣
መደገፊያውንም ከወርቅ ሠራ፤
መቀመጫውም በሐምራዊ ሐር የተሸፈነ ነው፤
ውስጡም በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፣
ፍቅር የተለበጠ ነው።#3፥10 ወይም የተለበጠውም ውስጥ፣ ከኢየሩሳሌም ቈነጃጅት የሆነ የፍቅር ስጦታ
11እናንተ የጽዮን ቈነጃጅት ውጡ፤
ንጉሥ ሰሎሞን አክሊሉን ደፍቶ እዩት፤
ዘውዱም ልቡ ሐሤት ባደረገባት፣
በዚያች በሰርጉ ዕለት፣
እናቱ የደፋችለት ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ