ዘካርያስ 3

3
ለሊቀ ካህኑ የሚሆን ንጹሕ ልብስ
1እርሱም ሊቀ ካህኑን ኢያሱን#3፥1 የየሽዋ ለሚለው ተለዋጭ ስም ነው፤ እዚህ ላይ እንዲሁም በዘካርያስ መጽሐፍ በሌሎች ቦታ።እግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ፣ ሰይጣንም#3፥1 ሰይጣንም ትርጕሙ “ከሳሽ” ማለት ነው። ሊከስሰው በስተ ቀኙ ቆሞ አሳየኝ። 2እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “አንተ ሰይጣን፤ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፤ ኢየሩሳሌምን የመረጠ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፤ ይህ ሰው ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን?” አለው።
3ኢያሱም ያደፈ ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ ነበር። 4መልአኩም ከፊቱ ቆመው የነበሩትን፣ “ያደፉ ልብሶቹን አውልቁለት” አላቸው።
ኢያሱንም፣ “እነሆ፤ ኀጢአትህን ከአንተ አስወግጃለሁ፤ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ” አለው።
5እኔም፣ “ንጹሕ ጥምጥም በራሱ ላይ አድርጉለት” አልሁ። የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ እያለ፣ ንጹሕ ጥምጥም በራሱ ላይ አደረጉለት፤ ልብስም አለበሱት።
6እግዚአብሔርም መልአክ ለኢያሱ ይህን ማስጠንቀቂያ ሰጠው፤ 7“የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በመንገዴ ብትሄድ፣ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፣ ቤቴን ታስተዳድራለህ፤ በአደባባዮቼም ላይ ኀላፊ ትሆናለህ፤ በዚህ በቆሙት መካከል ቦታ እሰጥሃለሁ።
8“ ‘ሊቀ ካህኑ ኢያሱ ሆይ፤ ስማ፤ በፊትህ የሚቀመጡትም ረዳቶችህ ገና ወደ ፊት ለሚመጡት ምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፤ እነሆ፤ ባሪያዬን ቍጥቋጡን አመጣለሁ። 9በኢያሱ ፊት ያስቀመጥሁት ድንጋይ እነሆ፤ በዚያ በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዐይኖች#3፥9 ወይም ገጾች አሉ፤ በርሱም ላይ ቅርጽ እቀርጻለሁ፤ የዚህችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር
10“ ‘በዚያ ቀን እያንዳንዱ በገዛ ወይኑና በለሱ ሥር ሆኖ ባልንጀራውን ይጋብዛል’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”

Currently Selected:

ዘካርያስ 3: NASV

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ