1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3
3
በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተከሠተ መለያየት
1ወንድሞቼ ሆይ! እኔ ሳስተምራችሁ ሥጋውያንና በክርስቶስ ገና ያልጠነከራችሁ ሕፃናት እንደ መሆናችሁ መጠን ነው እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ መጠን አይደለም። 2ጠንካራ ምግብ መብላት እንደማይችሉ ሕፃናት ስለ ሆናችሁ እኔ የመገብኳችሁ ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም፤ አሁንም ቢሆን ጠንካራ ምግብ መመገብ ገና የማትችሉ ናችሁ። #ዕብ. 5፥12-13። 3እናንተ አሁንም ገና ሥጋውያን ናችሁ፤ እርስ በርሳችሁ ስለምትቀናኑና ስለምትከራከሩ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? የምትሠሩትስ እንደ ተራ ሰው አይደለምን? 4አንዱ “እኔ የጳውሎስ ነኝ” ሌላው ደግሞ “እኔ የአጵሎስ ነኝ” ሲል ተራ የዓለም ሰዎች ብቻ መሆናችሁ አይደለምን? #1ቆሮ. 1፥12።
5ለመሆኑ አጵሎስ ምንድን ነው? ጳውሎስስ ምንድን ነው? እነርሱ እናንተ እንድታምኑ ያደረጉአችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ እያንዳንዳቸው የሚያገለግሉትም ጌታ ለያንዳንዳቸው በመደበላቸው ሥራ ነው፤ 6እኔ ተከልኩ፤ አጵሎስ ውሃ አጠጣ፤ ያሳደገው ግን እግዚአብሔር ነው። #ሐ.ሥ. 18፥4-11። 7ስለዚህ ለሥራው ዋና የሆነው ተክሉን ያሳደገው እግዚአብሔር ነው እንጂ የተከለም ሆነ ውሃ ያጠጣ ምንም አይደለም። 8የተከለም ሆነ ውሃ ያጠጣ እኩል ናቸው፤ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ዋጋውን ይቀበላል። 9እኛ ለእግዚአብሔር አብረን የምንሠራ አገልጋዮች ነን፤ እናንተም የእግዚአብሔር እርሻና የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችሁ። 10እግዚአብሔር በሰጠኝ ጸጋ መጠን እንደ ብልኅ ግንበኛ መሠረትን ጣልኩ፤ ሌላውም እኔ በጣልኩት መሠረት ላይ ይገነባል፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በዚያ ላይ እንዴት እንደሚገነባ መጠንቀቅ አለበት። 11አንድ ጊዜ ከተመሠረተው መሠረት በቀር ማንም ሌላ መሠረት መጣል አይችልም፤ ይህም መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። 12በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ፥ ወይም በብር በከበረ ድንጋይ፥ ወይም በእንጨት፥ በሣር ወይም በገለባ የሚገነባ ቢኖር 13የእያንዳንዱ ሰው ሥራ የሚገለጥበት የፍርድ ቀን ይመጣል፤ በዚያን ቀን የእያንዳንዱ ሰው ሥራ ምን ዐይነት እንደ ሆነ በእሳት ተፈትኖ ይገለጣል። 14አንድ ግንበኛ በመሠረቱ ላይ የሠራው ሥራ በእሳት ተፈትኖ ሳይጐዳ ጸንቶ ከቆመ ግንበኛው ዋጋውን ያገኛል። 15ሥራው በእሳት ተቃጥሎ የተደመሰሰበት ግንበኛ ግን ዋጋው ይቀርበታል፤ ይሁን እንጂ እርሱ ራሱ፥ በእሳት ውስጥ አልፎ ሳይቃጠል እንደሚቀር ሰው ይድናል።
16የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆናችሁንና የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችሁ መኖሩን አታውቁምን? #1ቆሮ. 6፥19፤ 2ቆሮ. 6፥16። 17እንግዲህ ሰው የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነው፤ ይህም ቤተ መቅደስ እናንተ ናችሁ።
18ማንም ራሱን አያታል፤ በዚህ ዓለም የጥበብ ደረጃ ጥበበኛ መስሎ የሚታይ ቢኖር የእግዚአብሔርን እውነተኛ ጥበብ እንዲያገኝ ራሱን እንደ ሞኝ ይቊጠር። 19የዚህ ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነው፤ ይህም፦ “እግዚአብሔር ጥበበኞችን በተንኰላቸው ይይዛቸዋል” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው። #ኢዮብ 5፥13። 20እንዲሁም፥ “ጌታ የጥበበኞች ሐሳብ ከንቱ መሆኑን ያውቃል” የሚል ተጽፎአል። #መዝ. 94፥11።
21ስለዚህ ሁሉ ነገር የእናንተ ስለ ሆነ ማንም በሰው አይመካ። 22ጳውሎስም ቢሆን አጵሎስም ቢሆን፥ ጴጥሮስም ቢሆን፥ ዓለምም ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ ሞትም ቢሆን፥ አሁን ያለውም ቢሆን፥ በኋላ የሚመጣውም ቢሆን፥ ሁሉም የእናንተ ነው። 23እናንተ ግን የክርስቶስ ልጆች ናችሁ፤ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ልጅ ነው።
Currently Selected:
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997