1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4
4
የክርስቶስ አገልጋዮች
1እንግዲህ ሰው ሁሉ እኛን የክርስቶስ አገልጋዮች እንደ ሆንን የእግዚአብሔርንም ምሥጢር የመግለጥ ኀላፊነት የተሰጠን ባለ ዐደራዎች እንደ ሆንን አድርጎ ሊቈጥረን ይገባል። 2ባለ ዐደራዎችም ታማኞች ሆነው መገኘት አለባቸው። 3ስለ እኔ የሆነ እንደ ሆነ እናንተም ብትፈርዱብኝ ወይም ሌላ ሰው ቢፈርድብኝ ምንም ግድ የለኝም፤ በእውነቱ እኔ በራሴ ላይ እንኳ መፍረድ አልችልም። 4እኔ እንደማውቀው ከሆነ ኅሊናዬ አይወቅሰኝም፤ ይህም እኔ ንጹሕ መሆኔን አያስረዳም፤ ነገር ግን በእኔ ላይ የሚፈርድ ጌታ ብቻ ነው። 5ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።
6ወንድሞች ሆይ! እናንተን ለመጥቀም ብዬ በዚህ ጉዳይ እኔንና አጵሎስን እንደ ምሳሌ አድርጌ ተናገርኩ፤ ይህንንም ያደረግኹት “ከተጻፈው አትለፍ” የሚለውን ምክር ትርጒሙን ከእኛ እንድትማሩ ብዬ ነው፤ ስለዚህ በአንድ ሰው መመካት ሌላውን ሰው ግን መናቅ አይገባችሁም። 7አንተ ከሌሎች በምን ትበልጣለህ? ከሌላ ያልተቀበልከውስ ነገር ምን አለ? ታዲያ፥ ሁሉን ነገር የተቀበልከው ከሌላ ከሆነ እንዳልተቀበለ ሰው ስለምን ትመካለህ?
8አሁንማ የሚያስፈልጋችሁን ነገር ሁሉ አግኝታችኋል፤ አሁንማ ሀብታሞች ሆናችኋል፤ ከእኛም ተለይታችሁ ነግሣችኋል፤ በእርግጥ ብትነግሡማ ኖሮ፥ እኛም ከእናንተ ጋር አብረን ስለምንነግሥ መንገሣችሁ መልካም በሆነ ነበር፤ 9እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት ተፈርዶባቸው ወደሚገደሉበት ቦታ ከሚወሰዱት ሰዎች መካከል የመጨረሻዎቹ ያደረገን ይመስለኛል፤ ከዚህም የተነሣ በዓለም ሁሉ በመላእክትም ሆነ በሰዎች ፊት እንደ ትርኢት ሆነን እንታያለን፤ 10እኛ ስለ ክርስቶስ ብለን ሞኞች ሆነናል፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጥበበኞች ሆናችኋል፤ እንዲሁም እኛ ደካሞች ሆነናል፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ሆናችኋል፤ እናንተ የተከበራችሁ ሆናችኋል፤ እኛ ግን የተዋረድን ሆነናል። 11አሁንም ቢሆን እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፤ እንጠማለን፤ እንራቈታለን፤ እንደበደባለን፤ መጠለያ በማጣት እንንከራተታለን። 12በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲረግሙን እንመርቃለን፤ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፤ #ሐ.ሥ. 18፥3። 13ሲሰድቡንና ስማችንን ሲያጠፉ በትሕትና እንመልስላቸዋለን፤ እስከ አሁን ድረስ የዚህ ዓለም ውዳቂና የምድር ጥራጊ ጒድፍ ሆነናል።
14እኔ ይህን የምጽፍላችሁ እንደ ተወደዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልመክራችሁ አስቤ ነው እንጂ ላሳፍራችሁ ብዬ አይደለም። 15ምንም እንኳ በክርስቶስ ብዙ መሪዎች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም፤ እኔ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ወንጌል ወልጄአችኋለሁ። 16ስለዚህ የእኔን ምሳሌነት እንድትከተሉ እለምናችኋለሁ። 17በዚህ ምክንያት የተወደደውንና የታመነውን በጌታ ልጄ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ፤ በየቦታውና በየአብያተ ክርስቲያኑ እንደማስተምረው እርሱ እኔ በክርስቶስ ያገኘሁትን የአዲስ ሕይወት መመሪያ ያሳስባችኋል። #1ቆሮ. 11፥1፤ ፊል. 3፥17።
18ነገር ግን ከእናንተ አንዳንዶቹ እኔ እናንተን ለመጐብኘት የማልመጣ መስሎአቸው በትዕቢት ተሞልተዋል። 19ይሁን እንጂ የጌታ ፈቃድ ቢሆን በቅርብ ጊዜ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ የእነዚህን ትዕቢተኞች ንግግራቸውን ብቻ ሳይሆን ኀይላቸውንም ማወቅ እፈልጋለሁ። 20የእግዚአብሔር መንግሥት የንግግር ጉዳይ ሳይሆን የእግዚአብሔር ኀይል ነው። 21የምትፈልጉት ምንድን ነው? የመቅጫ በትር ይዤ ወደ እናንተ እንድመጣ ትፈልጋላችሁን? ወይስ በፍቅርና በትሕትና መንፈስ እንድመጣ ትፈልጋላችሁ?
Currently Selected:
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997