አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል መግቢያ
መግቢያ
የመጀመሪያው መጽሐፈ ሳሙኤል፥ እስራኤል ከመሳፍንት አገዛዝ ወደ ንጉሣዊ መንግሥት የተሸጋገረችበትን ሁኔታ ይገልጣል፤ ይህ ለውጥ በእስራኤል ሊካሄድ የቻለው አብዛኛውን በሦስት ሰዎች ምክንያት ነው፤ እነርሱም፦ አንደኛው ከመጨረሻዎቹ ታላላቅ መሳፍንት አንዱ የነበረው ሳሙኤል ሲሆን፥ ሁለተኛው የእስራኤል የመጀመሪያ ንጉሥ የነበረው ሳኦል ነው፤ ሦስተኛው ደግሞ ወደ ሥልጣን ከመውጣቱ በፊት የነበረው የመጀመሪያ ታሪኩ ከሳሙኤልና ከሳኦል ታሪክ ጋር የተጣመረው ዳዊት ነው።
የዚህ መጽሐፍ ዋና መልእክት በብሉይ ኪዳን እንደሚገኙት እንደ ሌሎቹ የታሪክ መጻሕፍት ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን በረከትንና የኑሮ መሳካትን እንደሚያስከትል፥ ያለ መታዘዝም ውድቀትንና ጥፋትን እንደሚያመጣ ያሳያል። ይህም እግዚአብሔር ለካህኑ ለዔሊ፦ “እኔ የሚያከብሩኝን አከብራለሁ፤ የሚንቁኝንም አዋርዳለሁ” በማለት በተናገረው ቃል ግልጥ ሆኖ ይታያል (ም. 2፥30)።
ይህ መጽሐፍ ስለ ንጉሣዊ መንግሥት አመሠራረት የነበረውን የተለያየ ስሜት ይገልጣል፤ ቀደም ሲል የእስራኤል እውነተኛ ንጉሥ እንደ ሆነ የሚታወቀው ራሱ እግዚአብሔር ነበር፤ ነገር ግን ዘግየት ብሎ ከሕዝቡ በተነሣው ጥያቄ መሠረት፥ እግዚአብሔር ለእነርሱ ንጉሥ መረጠላቸው። ያም ሆነ ይህ ዋናው ቁምነገር ንጉሡም ሆነ፥ የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር የበላይነትና ፈራጅነት ሥር መገኘታቸው ነው ም. 2፥7-10። ይህም በእግዚአብሔር ሕግ ሥር ሀብታሞችም ሆኑ ድኾች የሰዎች መብት በትክክል መከበር እንዳለበት የሚያመለክት ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
ሳሙኤል የእስራኤል መሪ ስለ መሆኑ 1፥1—7፥17
የሳኦል መንገሥ 8፥1—10፥27
የመጀመሪያዎቹ የሳኦል አገዛዝ ዓመቶች 11፥1—15፥25
ዳዊትና ሳኦል 16፥1—30፥31
የሳኦልና የልጆቹ ሞት 31፥1-13
Currently Selected:
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997